Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-09-24 21:20:00
7.7K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:55:01
"ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እሁንም ለቀጠናው መረጋጋት ቁልፍ ሚና መጫወት ይችላሉ ብዬ አስባለሁ" - የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ

አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ሩቶ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "ለኢትዮጵያው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ ዐቢይ ሥልጣን ቢለቁ አይሻልም ወይ?" ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ "ዐቢይ እሁንም ለቀጠናው መረጋጋት ቁልፍ ሚና መጫወት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ" ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ሩቶ አክለውም ለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር አብረን እንሰራለን ሲሉ ተደምጠዋል። ተሰናባቹ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኬንያታን  "የቀጠናው ሰላም አፈላላጊ" አድርጌ የሾምኳቸው ልዩነታችን የፖለቲካ ፉክክር ብቻ ስለነበር ነው ብለዋል። 

wazema
• @ThinkAbyssinia •
3.8K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:00:59 #ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዞ የናይጄሪያ አየር መንገድን ለማቋቋም ተስማማ።

የራሷ ብሄራዊ አየር መንገድ የሌላት ናይጄሪያ ባለፉት ዓመታት የራሷን አየር መንገድ ለማቋቋም ለበርካታ የአፍሪካ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች የራሷን የአቪዬሽን ተቋም እንዲያቋቁሙላት ጥሪ ባቀረበችው መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ49 በመቶ ድርሻ የናይጀሪያ አየር መንገድን ለማቋቋም የወጣውን ውድድር ማሸነፉን ሮይተርስ ዘግቧል።

2፤ሲሚንቶ ከማከፋፈል የታገዱ ጅምላ ነጋዴዎች ኢኮኖሚያዊ ጫና እንደደረሰባቸው አስታወቁ።

ከወራት በፊት ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተጻፉ ደብዳቤዎች ሲሚንቶ ሲያከፋፍሉ የነበሩ ወኪሎች ከገበያ ስርዓቱ እንዲያስወጡ በታዘዙት መሠረት፣ ከገበያ ውጪ የሆኑ ወኪሎች በተላለፈባቸው ውሳኔ መሠረት ከፍተኛ ችግር እንደደረሰባቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

3፤በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዛሬ የሥራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ ተደረገ።

በከተማዋ የንግድ መደብሮች እና ባንኮች ተዘግተው እና የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጦ መዋሉን ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል። የከተማዋ ሕዝብ አድማ የመታበት ምክንያት፣ የጉራጌ ዞን የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ካለማግኘቱ ጋር የተያይዘ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። የደቡብ ክልል ጸጥታ ዕዝ የንግድ መደብሮችንና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ማቋረጥ ክልክል መሆኑን ትናንት አስጠንቅቆ ነበር።

4፤ሚኒስቴሩ በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ላይ መሆኑን ገለፀ።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የኃይል መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁሞ የመልሶ ግንባታ ሥራው የሚካሄደው ለዞንና በርካታ ቁጥር ላላቸው ከተሞች ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ነው ብሏል። በተለይም በህውሀት ወረራ ለተጎዱ አማራና አፋር ክልሎች ቅድሚ ይሰጣል ተብሏል።

5፤የጀርመን መራሄ መንግስት የገልፍ ሀራትን መጎብኘት ጀመሩ።

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ያጋጠማቸውን ነዳጅ ችግር ለመፍታት በሚል በዛሬው ዕለት በሪያድ ከሳውዲ አልጋወራፍ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር የመከሩ ሲሆን የውይይት አጀንዳቸው ነዳጅ እንደሆነ የጀርመን ድምጽ ዘግቧል፡፡ መራሄ መንግስቱ ሾልዝ ከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል ወደ አቡዳቢ እና ዶሃ በማቅናት ከሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ጋር እንደሚወያዩ ዘገባው አክሏል፡፡

6፤ወልቂጤ ከነማ የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫን አሸነፈ።

ክትፎዎቹ የዩጋንዳውን ክለብ ቡል ኤፍ ሲ 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻሉት። በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ወልቂጤ ከመመራት ተነስቶ በሳሙኤል አስፈሪ እና ጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች ማሸነፍ ችሏል። የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ በአራት የሀገር ውስጥ ክለቦች እና በሁለት ተጋባዥ የውጭ ሀገር ክለቦች መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አገኝቷል።

• @ThinkAbyssinia •
4.6K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 15:48:15
የ20 ጊዜ የግራንድ ስላም ሻምፒዮን አሸናፊው ሮጀር ፌደረር ራሱን ከቴኒስ አገለለ

ስዊዘርላንዳዊው ታሪክ አይሽሬ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ሮጀር ፌደረር ዛሬ ሌሊት የመጨረሻው ጨዋታውን በላቨር ካፕ ካደረገ በኋላ ራሱን ከውድድር አለም ማግለሉን አሳውቋል።

369 ጨዋታዎችን ያሸነፈው፤ 103 የኤቲፒ የነጠላ ውደድር ባለድል፤ የ2 ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ባለሜዳሊያ ፤ ለ237 ተከታታይ ሳምንት የአለም ቁጥር አንድ የተባለው የ20 ጊዜ የግራንድ ስላም ሻምፒዮን አሸናፊው ሮጀር ፌደረር በመጨረሻም ራኬቱን ሰቅሏል።

• @ThinkAbyssinia •
6.5K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 12:47:37
ከ1ኛ ክፍል እስከ ዶክተርነት ሕልማቸውን ያሳኩ 16 አብሮ አደጎች

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዘንድሮ በመጀመሪያ ዲግሪ ከሚያስመርቃቸው ከ250 ከሚበልጡ የሕክምና ተማሪዎች ውስጥ 16ቱ ከልጅነት ጀምሮ የሚተዋወቁ ወላይታ ሊቃ ከተባለ ትምህርት ቤት አብረው የመጡ ወጣቶች ናቸው። አብሮ አደገቹ ከለጋ ዕድሜያቸው አንስቶ ሐኪም የመሆን ልዩ ፍላጎት የነበራቸው ሲሆን፣ ሕልማቸውን እውን ለማድረግም አብሮ በማጥናት እና በመደጋገፍ ሲተጉ መቆየታቸውን ይገልጻሉ።

አብሮ አደገቹ ሐኪሞች ዩኒቨርስቲ ከገቡም በኋላ ግንኙነታቸው ይበልጥ ተጠናክሮ ያለፉትን 7 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በብርቱ ወንድማማችነት ያሳለፉ ሲሆን፣ በግቢ ቆይታቸውም የሕክምና ትምህርት የሚጠይቀውን ትዕግሥት እና ትጋት ማዳበራቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

• @ThinkAbyssinia •
7.8K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 12:28:06
ሸኔ ከሰሞኑ በወለጋ ሆሮጉድሩ በንጹሀን ላይ ግድያ መፈፀሙን መንግስት ገለፀ

ከሰሞኑ በወለጋ ሆሮጉድሩ በንጹሀን እና በሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ የተፈጸመዉ በሸኔ መሆኑን መንግስት ተናግሯል። ቡድኑ በመንግስት የተገደሉትን ጃል ኡርጂ የተባሉትን የቡድኑ አዛዥ ደም በመበቀል ነዉ ብሏል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን በጉዳዩ ላይ ያወጣው ሙሉ መግለጫ ከላይ ይመልከቱት።

• @ThinkAbyssinia •
7.3K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 11:16:08
ፀደይ ባንክ በመላው ሀገሪቱ ስራ ጀመረ

የቀድሞው የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የአሁኑ የፀደይ ባንክ በ148 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በ8 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል በመያዝ በዛሬው ዕለት በመላው ሀገሪቱ ሥራ እንደጀመረ በዛሬው ዕለት በተከናወነው የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ላይ ተገልጿል።

• @ThinkAbyssinia •
7.5K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 11:15:55 Think አቢሲንያ pinned a GIF
08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 11:13:42
ኪያድ ዳቦ እና ኬክ
Kiyad Bakery and Coffee

ለልደት፣ ለሰርግ እና ለምርቃት በፈለጉት ዲዛይን እና መጠን እናዘጋጃለን።

Bring us your cake designs! We prepare cakes for every occasion!

0911467026
0913911679

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

https://t.me/kiyad_bakery

አድራሻ: ልደታ ፍሊንት ስቶን አካባቢ
      የልደታ የፍታብሔር ምድብ ችሎት ፊት ለፊት

https://maps.app.goo.gl/4hYtermcawkxksDH7
7.1K viewsedited  08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 10:27:22 #ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃ የዝግጅት ስራው እየተገባደደ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ ተቋማት እና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ የበኩሉን እንዲያደርግ የሲቪክ ማህበራቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

2፤በትግራይ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸው ተነገረ።

በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት መጠን በመቀነሱ በክትባት መከላከል የሚቻሉ ልጆችን የሚያጠቁ ኩፍኝን፣ ፖሊዮን እና ቲታነስን የመሳሰሉ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸውን የክልሉ የጤና ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል። የትግራይ ጤና ቢሮ በክልሉ መደበኛ የበሽታዎች መከላከያ ክትባቶችን የሚያገኙ ልጆች መጠን ከ10 በመቶ በታች አሽቆልቁሏል ብሏል።

3፤የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አልሻባብ ከሶማሊያ ምድር እንደሚወገድ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናገሩ።


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ፤ መንግስታቸው አልሻባብን ከሶማሊያ እንደሚያስወግድ እርግጠኛ መሆናቸውን የተናገሩት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር  ሲሆን፤ የሶማሊያን ህዝብ በማስተባበር ሽብርተኝነት ከሶማሊያ ምድር እናስወግዳለን ብለዋል፡፡ አልሻባብ ከሶማሊያ ባለፈ የቀጠናው ስጋት መሆኑ ይታወቃል፡፡

4፤ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ገና አለመወሰናቸውን ገለፁ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሲቢኤስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት “በድጋሜ የመመረጥ ዓላማ ቢኖረኝም አሁን ላይ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ይበሉ እንጅ፤ ዋይት ሀውስ ጆ- ባይደን በ2024ቱ ምርጫ እንደገና እንደሚወዳደሩ ደጋግሞ ሲገልጽ የቆየ ሲሆን አብዛኞቹ ዴሞክራቶች ደግሞ ከጆ ባይደን ይልቅ ሌላ ሰው እንዲወዳደር ይፈልጋሉ መባሉ ይታወሳል።

5፤መቻል በፍፃሜው ጨዋታ አልሳተፍም ሲል ገለፀ።

የመዲናዋ ክለብ የሆነው መቻል እግርኳስ ክለብ ለአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍፃሜ ቢደርስም የከታማ አስተዳደሩ ስላስቀየመን በፍፃሜው አልሳተፍም ሲል ገልጸዋል። ክለቡ ይህንን ያለው ትላንት የከተማ አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእያንዳንዳቸው የ10 ሚልዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

• @ThinkAbyssinia •
6.6K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ