Get Mystery Box with random crypto!

#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች 1፤ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ። | Think Abyssinia

#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃ የዝግጅት ስራው እየተገባደደ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ ተቋማት እና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ የበኩሉን እንዲያደርግ የሲቪክ ማህበራቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

2፤በትግራይ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸው ተነገረ።

በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት መጠን በመቀነሱ በክትባት መከላከል የሚቻሉ ልጆችን የሚያጠቁ ኩፍኝን፣ ፖሊዮን እና ቲታነስን የመሳሰሉ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸውን የክልሉ የጤና ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል። የትግራይ ጤና ቢሮ በክልሉ መደበኛ የበሽታዎች መከላከያ ክትባቶችን የሚያገኙ ልጆች መጠን ከ10 በመቶ በታች አሽቆልቁሏል ብሏል።

3፤የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አልሻባብ ከሶማሊያ ምድር እንደሚወገድ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናገሩ።


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ፤ መንግስታቸው አልሻባብን ከሶማሊያ እንደሚያስወግድ እርግጠኛ መሆናቸውን የተናገሩት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር  ሲሆን፤ የሶማሊያን ህዝብ በማስተባበር ሽብርተኝነት ከሶማሊያ ምድር እናስወግዳለን ብለዋል፡፡ አልሻባብ ከሶማሊያ ባለፈ የቀጠናው ስጋት መሆኑ ይታወቃል፡፡

4፤ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ገና አለመወሰናቸውን ገለፁ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሲቢኤስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት “በድጋሜ የመመረጥ ዓላማ ቢኖረኝም አሁን ላይ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ይበሉ እንጅ፤ ዋይት ሀውስ ጆ- ባይደን በ2024ቱ ምርጫ እንደገና እንደሚወዳደሩ ደጋግሞ ሲገልጽ የቆየ ሲሆን አብዛኞቹ ዴሞክራቶች ደግሞ ከጆ ባይደን ይልቅ ሌላ ሰው እንዲወዳደር ይፈልጋሉ መባሉ ይታወሳል።

5፤መቻል በፍፃሜው ጨዋታ አልሳተፍም ሲል ገለፀ።

የመዲናዋ ክለብ የሆነው መቻል እግርኳስ ክለብ ለአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍፃሜ ቢደርስም የከታማ አስተዳደሩ ስላስቀየመን በፍፃሜው አልሳተፍም ሲል ገልጸዋል። ክለቡ ይህንን ያለው ትላንት የከተማ አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእያንዳንዳቸው የ10 ሚልዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

• @ThinkAbyssinia •