Get Mystery Box with random crypto!

ከ1ኛ ክፍል እስከ ዶክተርነት ሕልማቸውን ያሳኩ 16 አብሮ አደጎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ | Think Abyssinia

ከ1ኛ ክፍል እስከ ዶክተርነት ሕልማቸውን ያሳኩ 16 አብሮ አደጎች

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዘንድሮ በመጀመሪያ ዲግሪ ከሚያስመርቃቸው ከ250 ከሚበልጡ የሕክምና ተማሪዎች ውስጥ 16ቱ ከልጅነት ጀምሮ የሚተዋወቁ ወላይታ ሊቃ ከተባለ ትምህርት ቤት አብረው የመጡ ወጣቶች ናቸው። አብሮ አደገቹ ከለጋ ዕድሜያቸው አንስቶ ሐኪም የመሆን ልዩ ፍላጎት የነበራቸው ሲሆን፣ ሕልማቸውን እውን ለማድረግም አብሮ በማጥናት እና በመደጋገፍ ሲተጉ መቆየታቸውን ይገልጻሉ።

አብሮ አደገቹ ሐኪሞች ዩኒቨርስቲ ከገቡም በኋላ ግንኙነታቸው ይበልጥ ተጠናክሮ ያለፉትን 7 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በብርቱ ወንድማማችነት ያሳለፉ ሲሆን፣ በግቢ ቆይታቸውም የሕክምና ትምህርት የሚጠይቀውን ትዕግሥት እና ትጋት ማዳበራቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

• @ThinkAbyssinia •