Get Mystery Box with random crypto!

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች 1፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዞ የናይጄሪያ | Think Abyssinia

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዞ የናይጄሪያ አየር መንገድን ለማቋቋም ተስማማ።

የራሷ ብሄራዊ አየር መንገድ የሌላት ናይጄሪያ ባለፉት ዓመታት የራሷን አየር መንገድ ለማቋቋም ለበርካታ የአፍሪካ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች የራሷን የአቪዬሽን ተቋም እንዲያቋቁሙላት ጥሪ ባቀረበችው መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ49 በመቶ ድርሻ የናይጀሪያ አየር መንገድን ለማቋቋም የወጣውን ውድድር ማሸነፉን ሮይተርስ ዘግቧል።

2፤ሲሚንቶ ከማከፋፈል የታገዱ ጅምላ ነጋዴዎች ኢኮኖሚያዊ ጫና እንደደረሰባቸው አስታወቁ።

ከወራት በፊት ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተጻፉ ደብዳቤዎች ሲሚንቶ ሲያከፋፍሉ የነበሩ ወኪሎች ከገበያ ስርዓቱ እንዲያስወጡ በታዘዙት መሠረት፣ ከገበያ ውጪ የሆኑ ወኪሎች በተላለፈባቸው ውሳኔ መሠረት ከፍተኛ ችግር እንደደረሰባቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

3፤በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዛሬ የሥራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ ተደረገ።

በከተማዋ የንግድ መደብሮች እና ባንኮች ተዘግተው እና የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጦ መዋሉን ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል። የከተማዋ ሕዝብ አድማ የመታበት ምክንያት፣ የጉራጌ ዞን የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ካለማግኘቱ ጋር የተያይዘ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። የደቡብ ክልል ጸጥታ ዕዝ የንግድ መደብሮችንና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ማቋረጥ ክልክል መሆኑን ትናንት አስጠንቅቆ ነበር።

4፤ሚኒስቴሩ በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ላይ መሆኑን ገለፀ።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የኃይል መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁሞ የመልሶ ግንባታ ሥራው የሚካሄደው ለዞንና በርካታ ቁጥር ላላቸው ከተሞች ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ነው ብሏል። በተለይም በህውሀት ወረራ ለተጎዱ አማራና አፋር ክልሎች ቅድሚ ይሰጣል ተብሏል።

5፤የጀርመን መራሄ መንግስት የገልፍ ሀራትን መጎብኘት ጀመሩ።

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ያጋጠማቸውን ነዳጅ ችግር ለመፍታት በሚል በዛሬው ዕለት በሪያድ ከሳውዲ አልጋወራፍ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር የመከሩ ሲሆን የውይይት አጀንዳቸው ነዳጅ እንደሆነ የጀርመን ድምጽ ዘግቧል፡፡ መራሄ መንግስቱ ሾልዝ ከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል ወደ አቡዳቢ እና ዶሃ በማቅናት ከሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ጋር እንደሚወያዩ ዘገባው አክሏል፡፡

6፤ወልቂጤ ከነማ የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫን አሸነፈ።

ክትፎዎቹ የዩጋንዳውን ክለብ ቡል ኤፍ ሲ 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻሉት። በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ወልቂጤ ከመመራት ተነስቶ በሳሙኤል አስፈሪ እና ጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች ማሸነፍ ችሏል። የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ በአራት የሀገር ውስጥ ክለቦች እና በሁለት ተጋባዥ የውጭ ሀገር ክለቦች መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አገኝቷል።

• @ThinkAbyssinia •