2022-09-23 09:57:04
#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች
1፤የዓለም ቱሪዝም ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ይከበራል።
የዓለም ቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 13 እስከ 15፣ በተለያዩ ኸነቶች ደምቆ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በአሶሳ ከተማ ይከበራል፡፡ በኢትዮጵያ ለ35ኛ ጊዜ ‘’አዲሥ እሳቤ ለቱሪዝም’’ በሚል መሪ ሃሳብ የባሕላዊ ፣ታሪካዊ፣ ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሯዊ መስህብ ሐብቶች ጉብኝት የሚደረግ ሲሆን፥ በተጨማሪም በዓሉ በኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም በአሶሳ ከተማና አካባቢዉ እንደሚከበር ከክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
2፤በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳይገጥማቸው በትኩረት እየተሠራ ነው ተባለ። በሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሌተናል ጄኔራል አናን ሃሚድ ሞሃመድ ኦማር እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ያሉ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳይገጥማቸው ጥያቄዎቻቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ የሀገራቱ መሪዎች ጭምር በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
3፤አዲስ አበባ 8ኛውን የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ መድረክ ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ነው።
ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የ8ኛው የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ የምጣኔ ሃብት የምክክር መድረክ ዝግጅት የሚያግዝ ውይይት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተካሄዷል። ውይይቱ ከዚህ ቀደም በፒተርስበርግ በተካሄደው 7ኛው የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ መድረክ የተወሰኑ፣ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ሚኒስትሩ የመንግስት አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
4፤አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ለአፍሪካ ሀገራት የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጠየቁ።አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የበለጸጉ ሀገራት እና አለምአቀፍ አበዳሪዎች በድሃ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ያሉ የዕዳ ጫናዎችን እንዲገመግሙ ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው ይህንን ጥሪ ያቀረቡት። በተለይ የአፍሪካ ሀገራት በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ጫናዎች እንደነበሩባቸውም ተናግረዋል።
5፤ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ ያደረኩት ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ድጋፍ የለም አለች።ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አድርጋለች መባሉን ያስተባበለች ሲሆን አሜሪካ የሀገሪቱን ስም ከማጠልሸት እንድትቆጠብም አስጠንቅቃለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓቴል "ሰሜን ኮርያ ለሩሲያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሮኬቶችን እና መድፎችን ግዥ እየፈጸች ነው" በማለት ከሳምንት በፊት መናገራቸውን ተከትሎ ነው ሰሜን ኮሪያ ማስተባበያ የሰጠችው፡፡
6፤ኢትዮጵያና ሱዳን የወዳጅነት ጨዋታቸውን ዛሬ ያካሂዳሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ከሚያደርጋቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች መካከል የመጀመሪያውን ዛሬ ረፋድ ሲያካሂድ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ደግሞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰአት ያደርጋል። በፊፋ ወርሃዊ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 138ኛ፤ ሱዳን ደግሞ 130ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
• @ThinkAbyssinia •
6.5K views06:57