2022-09-22 18:36:54
#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች
1፤የጉሙዝ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ የታጠቁ ወጣቶች ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ጠየቀ።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የጉሙዝ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ ማቅረቡን ዶቼቬሌ ዘግቧል። የፓርቲው ሊቀ መንበር ታጣቂዎቹ እና መንግሥት እርቅ ካደረጉበት ካለፈው ከመጋቢት ወር ጀምሮ በካማሺ እና መተከል ሰላም መፈጠሩን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
2፤አቶ ደመቀ መኮንን ከአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናያን ጋር በኒዉዮርክ ተገናኝተው መወያየታውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በወቅቱም የጋራ ተጠቃሚነትን የበለጠ ለማጠናከር ግንኙነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ሚኒስትቴሮቹ ተወያይተዋል።
3፤ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በመሰረተ ልማት ግንባታና የምጣኔ ሃብት ትስስር በጋራ ለመስራት ተስማሙ።የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ታባን ዴንግ ጋይ የተመራው ልዑክ ከኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጋር በሁሉቱ ሀገራት የመሰረተ ልማት ዝርጋታና ተጠቃሚነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ውይይቱን በማስመልከት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሁለቱ አገሮች በተለይም የመሰረተ ልማት ዝርጋታና ተጠቃሚነት ዙሪያ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
4፤የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ገብተዋል መባሉ ግጭቱን የበለጠ እንዲባባስ ያደርጋል ሲል የአውሮፓ ሕብረት አሳሰበ።የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ወደ ትግራይ ገብተዋል መባሉ ግጭቱን የበለጠ እንዲባባስ ያደርጋል ሲል የአውሮፓ ሕብረት አስቧል። የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ማንኛውንም ወታደራዊ መፍትሄ ወደ ጎን በመተው ለሕዝቦቻቸው ጥቅም ሲሉ ወደ ሰላም ጥረት እንዲመጡ ሕብረቱ በድጋሚ ያሳስባል ብለዋል።
5፤ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ52 ብር ከ5609 ሳንቲም ሲገዛ ውሏል።
እንዲሁም መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ6121 ሳንቲም መሆኑን ከድረገጹ ተመልክተናል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋው 56 ብር ከ9269 ሳንቲም እንዲሁም መሸጫው 58 ብር ከ0654 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ1562 ሳንቲም እየተገዛ በ53 ብር ከ1993 ሳንቲም የተሸጠ ሲሆን፣ አንድ የቻይና ዩዋን ደግሞ በ6 ብር ከ7499 ሳንቲም ተገዝቶ በ6 ብር ከ8849 ሳንቲም ሲሸጥ እንደነበር ቲንክአቢሲኒያ ተመልክቷል።
6፤የሊባኖስ ባንኮች ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቆሙ። የሊባኖስ ባንኮች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ጥበቃ አላደረጉልንም በሚል ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የአገሪቱ ባንኮች ማኅበር መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል። ደንበኞች ባለፈው ሳምንት እንዳይንቀሳቀስ የተደረገውን የቁጠባ ሂሳባቸውን ለማግኘት በኃይል ታግዘው ገንዘባቸውን የመውሰድ ድርጊቶች መበራከታቸውን ተከትሎ ነው የሊባኖስ ባንኮች ማኅበር አገልግሎት መቆሙን ያስታወቀው።
7፤ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቀቀ።በአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በአበበ በቂላ ስታዲየም ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባደረገው የማጣሪያ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይቷል። ብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኪንሻሳ ያደርጋል።
• @ThinkAbyssinia •
9.6K views15:36