Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 95

2022-05-04 15:57:36
አሸባሪው ህወሓት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን እያሰረ መሆኑ ተነገረ

ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባው አሸባሪው የህወሓት ቡድን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ልጆቻቸው ያልዘመቱ ወላጆችን እያሰረ እንደሚገኝ የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የትግራይ ተወላጅ ልጆቹ ለመዝመት ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ወላጅ አባቱ እና አጎቱ እንደታሰሩ ገልጿል።

ለራሱና ለቤተሰቡ ደኅንነት ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ወጣት፤ "ቢያንስ ከቤተሰብ አንድ ሰው ለውድትርና መላክ የሚል ሕግ አለ" ብሏል።


[BBC_Amharic]

• @ThinkAbyssinia •
7.8K viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 15:26:38
ትዊተር ድርጅቶች እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ክፍያ መጠየቅ ሊጀምር ነዉ ተባለ


ትዊተርን የግላቸዉ ለማድረግ በግዢ ሂደት ላይ ያሉት ባለፀጋው ኤለን መስክ ትዊተርን የሚገለገሉ ድርጅቶችን እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን/ ባለስልጣናትን የማስከፈል እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

የቴስላ እና የስፔስ ኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚው ኤለን መስክ ትዊተር ለመደበኛ ተገልጋዮች ግን ነፃ ሆኖ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የተጠየቀው ትዊተር ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠም፡፡

ኤለን መስክ ቀድሞዉኑ ወደ ግዢ ሂደቱ የገቡት በእንዲህ ያለ መንገድ የአገልግሎት ክፍያ ለመሰብሰብ አቅደው ነው ተብሏል፡፡ ለዚህም 44 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ለፈቀዱላቸው ባንኮች እንደማሳመኛ ይህንን ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ይህ የኤለን መስክ ውሳኔ ከፍተኛ ድንጋጤን እና አግራሞትን የፈጠረ ሲሆን ሌሎች ማሻሻያዎችም ሊከተሉ እንደሚችሉ መናገራቸዉን አር ቲ ዘግቧል፡፡

[RT_News]
• @ThinkAbyssinia •
8.0K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 12:49:29
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት መርሳቢት ግዛት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት መርሳቢት ግዛት ላንድ ወር ከምሽት እስከ ንጋት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታወጀው፣ በግዛቲቷ እየተባባሰ የሄደውን የጎሳ ግጭት እና የተደራጁ ቡድኖች ውንብድና
ለመቆጣጠር ሲሆን፣ ጸጥታ ኃይሎችም ሕገወጥ ጦር መሳሪያዎችን እንዲነጥቁ ታዘዋል።


መንግሥት የጎሳ ፖለቲከኞች የሚያስታጥቋቸው ሚሊሻዎች ግዛቲቱን የግጭት እና የአለመረጋጋት ቀጠና አድርገዋታል ሲልም ይከሳል።


• @ThinkAbyssinia •
8.9K views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 12:04:15
የአለም ዋንጫ ግንቦት 16 እና 17 ወደ ሀገራችን ይመጣል

የኳታሩ የአለም ዋንጫ ከመጀመሩ አስቀድሞ የ አለም ዋንጫ ለእይታ ከሚቀርቡባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሀገራችን ቀዳሚዋ ስትሆን በአሁን ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል በጉዳዩ ላይ እየተሰጠ በሚገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ የአለም ዋንጫው ወደ ሀገራችን መቶ የሁለት ቀን ቆይታ እንደሚኖረው ተገልጿል ።

የአለም ዋንጫው ወደ ሀገራችን ግንቦት 16 እና 17 የሚሙጣ ሲሆን ፈረንሳዊው ታላቅ ተጫዋች ወደ ሀገራችን እንደሚመጣ ይፋ ሆኗል ።

የ 1998 የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ የፊት መስመር አጥቂ ዴቪድ ትሪዝጌት ወደ ሀገራችን የሚመጣው ተጫዋች መሆኑ ይፋ ተደርጓል ።

ስልሳ ዓመታትን በሀገራችን መስራት የቻለው ኮካ ኮላ ወደ ሀገራችን " እውነተኛውን ዋንጫ " ለሶስተኛ ጊዜ የሚያመጣ ይሆናል ።


• @ThinkAbyssinia •
8.7K viewsedited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 11:49:11
ዩክሬን የኔቶ እቅዶቿን አሁንም እንዳልተወችው አሳወቀች

ኪየቭ የህብረቱ ቸልተኝነት የመተቸት ሙሉ መብት አላት ሲሉ የዩክሬን የአውሮፓ እና የዩሮ-አትላንቲክ ውህደት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦልጋ ስቴፋኒሺና ለኤል ፓይስ ተናግሯል። አክለውም ዩክሬን ወደ ህብረቱ የመቀላቀል አላማዋን "አትተወውም" ብለዋል ።

“ስዊድን እና ፊንላንድ በተቻለ ፍጥነት የኔቶ አባል ይሆናሉ። ነገር ግን በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ እነዚህ አገሮች ለአባልነት ውሳኔ ተጨማሪ 15 ዓመታት ቢጠብቁ እነሱም ወደ ጦርነት ውስጥ እንደሚገቡ እርግጥ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ስቴፋኒሺና በቃለ መጠይቁ ላይ ኪየቭ በዚህ ሳምንት ሁለተኛውን ክፍል አባልነት ጥያቄ እንደምታቀርብ ገልፀዋል።

[RT_News]
• @ThinkAbyssinia •
8.4K viewsedited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 10:32:39
#ቲንክአቢሲኒያ_የውጭምንዛሬ_መረጃዎች

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ አንድ የዶላር መግዣ ዋጋ 51 ብር ከ4167 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 52 ብር ከ4450 ሳንቲም ሆኖ እያገበያየ እንደሚገኝ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ
መግዣ ዋጋ ደሞ 61 ብር ከ6291 ሳንቲም እንዲሁም መሸጫው 62 ብር ከ8617 ሳንቲም
ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ54 ብር ከ3115 ሳንቲም ሲገዛ እና በ55 ብር ከ3977 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን፣ አንድ የቻይና ዩዋን ደሞ በ7 ብር ከ0407 ሳንቲም ሲገዛ እና
በ7 ብር ከ1815 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሚገኝ ቲንክቢሲኒያ ተመልክቷል።


• @ThinkAbyssinia •
8.6K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 10:30:49 #ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ክብርት ሀና ሰርዋ ቴቴ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
አምባሳደር ታዬ በቀጣናው ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በተወሰደው የተኩስ ማቆም ውሳኔ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ፤በቀጣናው ባሉ ድንበር ዘለል የፀጥታ ፈተናዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በቲዊተር ገጻቸዉ አስፍረዋል።


2፤የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል እንደሚሰሩ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ገለጹ።

በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከዋሽንግተን ዲሲ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
የሚሲዮኑ ባልደረቦች ዋና ትኩረት ዘመናትን ያስቆጠረው የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረግ እንደሚያሰፊልግ ተገልጸዋል።
በዳያስፖራ ተሳትፎ፣ ህዝብ ለህዝብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ገጽታ ግንባታ፣ ቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጎልበት እንደሚገባም ገልጸዋል።

3፤ሁለቱ ኮሚሽኖች ሥራቸውን ለአዲሱ የምክክር ኮሚሽን አስረከቡ።

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች እንዲሁም ሀገራዊ የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽኖች የሥራ ኃላፊነታቸውንና ሰነዶቻቸውን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች በተገኙበት ለአዲሱ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ኮሚሽኖቹ ብዙ ፈተናዎችን መሻገራቸውን ገልጸው፣ በቂ ክትትልና ድጋፍ ቢደረግላቸው ካከናወኗቸው ተግባራት በላይ መሥራት ይችሉ እንደነበር አስታውሰዋል።
በመሆኑም እነርሱ ካለፉበት ሁኔታ ትምህርት በመቅሰም፣ ለአሁኑ የምክክር ኮሚሽን አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ መደረግ እንዳለበት አፈ-ጉባዔው ገልጸዋል።


4፤የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6 ዙር አንደኛ የስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣ ተጨማሪ በጀት ማፅደቅና አዳዲስ ሹመቶችን ያከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የክልሉ የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ነው የተባለው፡፡

5፤አልሸባብ 170 የአፍሪካ ህብረት ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ።

የአልሸባብ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ሶማሊያ የብሩንዲ ወታደሮች በሚገኙበት የአፍሪካ ህብረት ጦር ሰፈር ላይ ኢላማ በማድረግ በሰነዘሩት ጥቃት ከ170 በላይ የብሩንዲ ወታደሮችን መግደላቸውን አስታውቋል። ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሰሜን ምስራቅ 130 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የጦር ሰፈር ከባድ ውጊያ እንደነበር የዜና ኤጀንሲዎች የዓይን እማኞችን ጠቅሰዉ ዘግበዋል።
የአፍሪካ ህብረት ጦር እየተባለ የሚጠራው እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ማለትም ከኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወታደሮችን ያቀፈ ስብስብ ነው።የሞቃዲሾን መንግስት ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር የሚያደርገውን ውጊያ የአፍሪካ ህብረት ጦር እየደገፈ ሲሆን በአልሻባብ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደምም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ይታወሳል፡፡


6፤ የሮማው ጳጳስ አባ ፍራሴስ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ለመገናኘት ያቀረቡት ጥያቄ እስከሁን ምላሽ እንዳላገኘ ተገለፀ።

ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ ተገናኝቶ ለመምከር ጥያቄ ማቅረባቸውን የሮማ ጳጳስ እና የዓለም ካቶሊካውያን አባት ተናግረዋል።
ከጣሊያኑ ኮሬ ዴላ ሴራ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ሞስኮው መምጣት እፈልጋለሁ ሲሉ ለፑቲን መልዕክት መላካቸውን ተናግረዋል። ሆኖም እስካሁን ለጥያቄው ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፤ አሁንም እየሞከሩ መሆናቸውን ጠቁመዋም።

7፤ሊቨርፑል የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በስታዲዮ ዴ ላ ሴራሚካ ቀጥሎ ሲካሄድ ሊቨርፑል 3-2 ሲያሸንፍ በድምር ውጤት ቪያሪያልን 5 - 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል ።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ፋቢኒሆ ፣ ሊዊስ ዲያዝ እና ሳዲዮ ማኔ አስቆጥረዋል ።
ሊቨርፑል የማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድን አሸናፊ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይገጥማል ።
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ግንቦት 20 በፈረንሳይ ርዕሰ መዲና ፓሪስ የሚካሄድ ይሆናል ።


• @ThinkAbyssinia •
8.7K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 08:11:23
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ
በሜት ጋላ ደምቀው አምሽቷዋል


ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ
ትላንት ምሽት በአሜሪካ በተካሄደው ሜት ጋላ የፋሽን ፕሮግራም ላይ እጅግ በጣም ቆንጆ ከሆኑ ጥንዶች አንዱ ተብለውም ተሰይመዋል።

በእለቱ ጥንዶቹ በኢትዮጵያዊያን የክብር አልባሳት (ንግሥት ሳባ ቀሚስ እና ካባ) የደመቁ ሲሆን ከኢትዮጵያውያንም ሙገሳ ተችሯቸዋል።

ዘ ሜት ጋላ የተሰኘው ፕሮግራም በኒውዮርክ ከተማ ለሚገኘው የሜትሮፖሊታን ሙዚየም የስነጥበብ አልባሳት ተቋም ጥቅም የሚውል ዓመታዊ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅት ነው። በዓለም ላይ በጣም ታዋቂው የፋሽን ዝግጅት ተብሎ በሰፊው የሚታወቅ ሲሆን በእለቱ እንደ ፋሽን፣ ፊልም፣ ቴሌቪዥን፣ ሙዚቃ፣ ስፖርት እና ማህበራዊ ሚዲያ ያሉ ታዋቂ ሰዎች በዚህ የፋሽን ዝግጅት ላይ ይጋበዛሉ።

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ ኢትዮጵያን በትልቅ መድረክ ሲያስጠሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ከዚህ ቀደምም በአባይ ጉዳይ ለአለም እውነታው ለማሳየት በብዙ ሲጥሩም ነበር።


• @ThinkAbyssinia •
10.0K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 22:54:53
ከላይ እንዳስቀመጥነው መረጃ አይነት የአዲስ አበባን እና ሌሎች የአፍሪካ ከተሞችን ንፅፅር እንዲሰራ ይፈልጋሉ ?
ከ 10ሺ በላይ ይስራ የሚሉ ድምፆች ካገኘን በየቀኑ 1 ንፅፅር የምንሰራ ይሆናል።
ለወዳጅዎ ያጋሩ!!
Anonymous Poll
91%
አዎ ይስራ
9%
ፍላጎቱ የለኝም
1.6K voters11.1K views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 21:38:28
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መንግስት ታጣቂዎችን ለመዋጋት በሚያደርገው ሂደት ውስጥ የንጹኃን ዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታውን መወጣት አልቻለም ሲሉ ኦፌኮ እና ኦነግ ወቀሱ።

ፓርቲዎቹ ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ብለዋል።በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ስፍራዎች እንዲሁም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ንጹሃንን ያልለዩ ግድያዎች ይፈጸማሉም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ንጹሃን ዜጎችን ደኅንነት እንደሚጠብቅ በመግለጥ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላት ጭምር ከተገደሉት ውስጥ ይገኙበታል ብሏል። 

[DW]

• @ThinkAbyssinia •
11.9K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ