Get Mystery Box with random crypto!

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ በሜት ጋላ ደምቀው አምሽቷዋ | Think Abyssinia

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ
በሜት ጋላ ደምቀው አምሽቷዋል


ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ
ትላንት ምሽት በአሜሪካ በተካሄደው ሜት ጋላ የፋሽን ፕሮግራም ላይ እጅግ በጣም ቆንጆ ከሆኑ ጥንዶች አንዱ ተብለውም ተሰይመዋል።

በእለቱ ጥንዶቹ በኢትዮጵያዊያን የክብር አልባሳት (ንግሥት ሳባ ቀሚስ እና ካባ) የደመቁ ሲሆን ከኢትዮጵያውያንም ሙገሳ ተችሯቸዋል።

ዘ ሜት ጋላ የተሰኘው ፕሮግራም በኒውዮርክ ከተማ ለሚገኘው የሜትሮፖሊታን ሙዚየም የስነጥበብ አልባሳት ተቋም ጥቅም የሚውል ዓመታዊ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅት ነው። በዓለም ላይ በጣም ታዋቂው የፋሽን ዝግጅት ተብሎ በሰፊው የሚታወቅ ሲሆን በእለቱ እንደ ፋሽን፣ ፊልም፣ ቴሌቪዥን፣ ሙዚቃ፣ ስፖርት እና ማህበራዊ ሚዲያ ያሉ ታዋቂ ሰዎች በዚህ የፋሽን ዝግጅት ላይ ይጋበዛሉ።

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰንና ባለቤቱ ሞዴል ማያ ሀይሌ ኢትዮጵያን በትልቅ መድረክ ሲያስጠሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ከዚህ ቀደምም በአባይ ጉዳይ ለአለም እውነታው ለማሳየት በብዙ ሲጥሩም ነበር።


• @ThinkAbyssinia •