Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ህወሓት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን እያሰረ መሆኑ ተነገረ ከኢትዮጵያ ጋ | Think Abyssinia

አሸባሪው ህወሓት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን እያሰረ መሆኑ ተነገረ

ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባው አሸባሪው የህወሓት ቡድን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ልጆቻቸው ያልዘመቱ ወላጆችን እያሰረ እንደሚገኝ የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የትግራይ ተወላጅ ልጆቹ ለመዝመት ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ወላጅ አባቱ እና አጎቱ እንደታሰሩ ገልጿል።

ለራሱና ለቤተሰቡ ደኅንነት ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ወጣት፤ "ቢያንስ ከቤተሰብ አንድ ሰው ለውድትርና መላክ የሚል ሕግ አለ" ብሏል።


[BBC_Amharic]

• @ThinkAbyssinia •