Get Mystery Box with random crypto!

ትዊተር ድርጅቶች እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ክፍያ መጠየቅ ሊጀምር ነዉ ተባለ ትዊተር | Think Abyssinia

ትዊተር ድርጅቶች እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ክፍያ መጠየቅ ሊጀምር ነዉ ተባለ


ትዊተርን የግላቸዉ ለማድረግ በግዢ ሂደት ላይ ያሉት ባለፀጋው ኤለን መስክ ትዊተርን የሚገለገሉ ድርጅቶችን እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን/ ባለስልጣናትን የማስከፈል እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

የቴስላ እና የስፔስ ኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚው ኤለን መስክ ትዊተር ለመደበኛ ተገልጋዮች ግን ነፃ ሆኖ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የተጠየቀው ትዊተር ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠም፡፡

ኤለን መስክ ቀድሞዉኑ ወደ ግዢ ሂደቱ የገቡት በእንዲህ ያለ መንገድ የአገልግሎት ክፍያ ለመሰብሰብ አቅደው ነው ተብሏል፡፡ ለዚህም 44 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ለፈቀዱላቸው ባንኮች እንደማሳመኛ ይህንን ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ይህ የኤለን መስክ ውሳኔ ከፍተኛ ድንጋጤን እና አግራሞትን የፈጠረ ሲሆን ሌሎች ማሻሻያዎችም ሊከተሉ እንደሚችሉ መናገራቸዉን አር ቲ ዘግቧል፡፡

[RT_News]
• @ThinkAbyssinia •