Get Mystery Box with random crypto!

የአለም ዋንጫ ግንቦት 16 እና 17 ወደ ሀገራችን ይመጣል የኳታሩ የአለም ዋንጫ ከመጀመሩ አስ | Think Abyssinia

የአለም ዋንጫ ግንቦት 16 እና 17 ወደ ሀገራችን ይመጣል

የኳታሩ የአለም ዋንጫ ከመጀመሩ አስቀድሞ የ አለም ዋንጫ ለእይታ ከሚቀርቡባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሀገራችን ቀዳሚዋ ስትሆን በአሁን ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል በጉዳዩ ላይ እየተሰጠ በሚገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ የአለም ዋንጫው ወደ ሀገራችን መቶ የሁለት ቀን ቆይታ እንደሚኖረው ተገልጿል ።

የአለም ዋንጫው ወደ ሀገራችን ግንቦት 16 እና 17 የሚሙጣ ሲሆን ፈረንሳዊው ታላቅ ተጫዋች ወደ ሀገራችን እንደሚመጣ ይፋ ሆኗል ።

የ 1998 የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ የፊት መስመር አጥቂ ዴቪድ ትሪዝጌት ወደ ሀገራችን የሚመጣው ተጫዋች መሆኑ ይፋ ተደርጓል ።

ስልሳ ዓመታትን በሀገራችን መስራት የቻለው ኮካ ኮላ ወደ ሀገራችን " እውነተኛውን ዋንጫ " ለሶስተኛ ጊዜ የሚያመጣ ይሆናል ።


• @ThinkAbyssinia •