2022-05-17 10:17:41
#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች
1፤በአዲስ አበባ 30 ሺህ ብቻ የነበረ የስደተኞች ቁጥር አሁን ላይ ወደ 80 ሺህ አሻቅቧል ተብለዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት ወደ ከተማ የሚገቡየስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ እንዲያሻቅብ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤን ኤች ሲአር) አስታወቀ። በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ ማማዱ ዲያን (ዶ/ር) እንደገለፁት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኖች ወደ አዲስ አበባና ሌሎች አካባዎች ለመሰደድ መገደዳቸውን የተገለፁ ሲሆን በተፈጠረው የጸጥታ ቀውስ ምክንያት በቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ የወደመው የጉሬ ሾምቦላ መጠለያ ጣቢያን ጨምሮ ከሌሎች መጠለያ ጣቢያዎች ሸሽተው የመጡ በርካታ ስደተኞች በአዲስ አበባ ይገኛሉም ብለዋል። ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ 30 ሺህ የነበረው የስደተኞች ቁጥር አሁን ላይ 80 ሺህ መድረሱንም የድርጅቱ ተወካይ ገልጸዋል።
2፤ለሁለኛው ዙር የኢድ እስከ ኢድ ዝግጅት ስኬት ሁሉም ባለድርሻ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ።ሰኔ 24 ለሚጀመረው ሁለኛው ዙር የኢድ እስከ ኢድ ዝግጅት የኢትዮጵያን ገፅታ ይበልጥ ለማስተዋወቅ በሚያስችል ደረጃ እንዲዘጋጅ ሁሉም ባለድርሻ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ። ከኢድ እስከ ኢድ ክብረ በአል የመርሃ ግብሮች አፈፃፀም፣ የእስካሁን ስራዎች እና ቀጣይ ተግባራትን የገመገመ ውይይት ብሄራዊ ፈፃሚ ኮሚቴው ትላንት በበይነ መረብ አከናውኗል። በውይይቱ የተገኘው ተሞክሮም የሁለተኛው ዙር ስራዎችን በላቀ ሁኔታ ለማከናወን እገዛ እንደሚኖረውም ተመሌክቷል። በቀጣይ መርሃ ግብር የተያዙ ታላላቅ ሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ መርሃ ግብሮች እንዳሉም ጠቁመዋል።
3፤ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ51 ብር ከ4841 ሳንቲም እየተገዛ ይገኛል።
እንዲሁም መሸጫ ዋጋው 52 ብር ከ5138 ሳንቲም መሆኑን ከድረገጹ ተመልክተናል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋው 60 ብር ከ3037 ሳንቲም እንዲሁም መሸጫው 61 ብር ከ5098 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ53 ብር ከ7385 ሳንቲም እየገዛ በ54 ብር ከ7929 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን፣ አንድ የቻይና ዩዋን ደግሞ በ6 ብር ከ8576 ሳንቲም ተገዝቶ በ6 ብር ከ9948 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሚገኝ ቲንክአቢሲኒያ ተመልክቷል።
4፤ቱርክ ስዊድንና ፊንላንድ ኔቶን እንዳይቀላቀሉ አስጠነቀቀች።የቱርክ ፕሬዝዳንት ራሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ሁለቱ የስካንዲኒቪያን አገራት ኔቶን ለመቀላቀል የሚያደርጉትን ሩጫ እንደሚቃወሙ ዝተዋል። ኤርዶጋን ይህን ያሉት ስዊድንና ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል በይፋ መወሰናቸውን ባስታወቁ በሰዓታት ውስጥ ነው። የሩሲያው ፑቲን በበኩላቸው ፊንላድና ስዊድን የጦር ቃል ኪዳን ድርጅቱን መቀላቀላቸው ሞስኮን ያን ያህልም እንደማያስጨንቃት፣ ቀጥተኛም ጉዳት እንደማያደርስባት ተናግረዋል። ኤርዶጋን ትናንት ሰኞ በሰጡት በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የስዊድንን እና የፊንላንድን ወደ ኔቶ መምጣት በበጎ እንደማያዩት ብሎም እንደሚቃወሙት ዝተዋል። ሁለቱ አገሮች አሸባሪ አቃፊ ናቸው ሲሉም ወርፈዋቸዋል።
5፤ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አሕጉራዊ የብድር ከፋይነት ደረጃ አውጪ ድርጅት እንዲቋቋም ጥሪ አቀረቡ።የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አሕጉራዊ የብድር
ከፋይነት ደረጃ አውጪ ድርጅት እንዲቋቋም ጥሪ ማድረጋቸውን የተለያዪ የዜና ምንጮች
ዘግበዋል። ዓለማቀፍ ደረጃ አውጪ ድርጅቶች ለአፍሪካ የሚሰጡት ግምገማ አገራቱ ብድር
እንዳያገኙ አድርጓል በማለት ሳል አማረዋል። በተወሰነ መጠን ትላልቆቹ ድርጅቶች ለአፍሪካ
አገራት ግምገማ ጥቅም ላይ የሚያውሏቸው ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸው መስፈርቶች
እንደሆኑ ማኪ ሳል ጠቁመዋል።
6፤አርሰናል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ የመሳተፍ እድሉን አጥብቧል።ትላንት ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰላሳ ሰባተኛው ሳምንት ጨዋታ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ቀጥሎ ሲካሄድ አርሰናል ከ ኒውካስትል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 - 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ። የኒውካስትልን የማሸነፊያ ግብ ቤን ኋይት በራሱ መረብ ላይ እና ብሩኖ ጉማሬስ አስቆጥረዋል ። ቤን ኋይት በዘንድሮ የውድድር አመት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ መረብ ላይ ግብ አስቆጥሯል ። አርሰናል በኒውካስትል ሽንፈትን ማስተናገዱን ተከትሎ ቼልሲ በቀጣዩ የውድድር አመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ መሳተፉን አረጋግጧል ። በቀጣይ እሁድ አርሰናል ከ ኤቨርተን እንዲሁም ቶተንሀም ከ ኖርዊች ሲቲ ጋር የሚገናኙ ይሆናል ። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ 66 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀምጥ ኒውካስትል በ 46 ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።
• @ThinkAbyssinia •
8.7K views07:17