2022-05-12 10:22:11
#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች
1፤የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የማስጀመሪያ መርሃግብር መካሄድ ጀመረ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የማስጀመሪያ መርሃግብር በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው። በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላት መምህራን፣ ተማሪዎች እና አመራሮች ተሳትፈዋል:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳድር ዲና ሙፍቲ ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ ለሀገር ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን እያበረከት አመታትን የዘለቀ ነው ብለዋል:: መርሀግብሩ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ሁሉም ዜጎች በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ለሀገራቸው እንዴት መሞገት እና ተጽዕኖ ማሳደር እንደሚችሉ ተማሪዎችን ማብቃት እንደሚገባም ተናግረዋል።
2፤በትግራይ ክልል ላይ የጣለው እገዳ እንዲነሳ እና ዕርዳታ እንዲገባ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ጠየቁ።የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት በትግራይ ክልል ላይ የጣሉትን እገዳ እንዲያነሱ እና ዕርዳታ እንዲገባ እንዲፈቅዱ በድጋሚ እጠይቃለሁ ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ተኩስ ካቆሙ 10 ሳምንታት እንደሆናቸው የገለጡት ዶ/ር ቴዎድሮስ፣
እስካሁን ወደ ትግራይ የገባው ዕርዳታ ግን 5 በመቶ ብቻ ነው ብለዋል።
3፤መንግሥት የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት ተገለጸ።መንግሥት የዜጎችን ደህንነትና መብት ለማስጠበቅ የጀመረውን አጥፊዎችን ለሕግ የማቅረብ እርምጃና ችግሩ በሌላ ጊዜ እንዳይደገም ከመሠረቱ የመከላከል ሥራን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገልጸዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ በአገሪቱ የሕግ የበላይነትን በማስጠበቅ ዙሪያ ምን መደረግ አለበት ለሚል ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት በኢትዮጵያ በየጊዜው እየታየ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ መንግሥት የጀመረውን የዜጎችን መብትና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት። በየጊዜው እየታየ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለመከላከል የመንግሥት ዋና ሥራና ትኩረት የዜጎችን መብትና ደኅንነት መጠበቅ መሆን ይኖርበታል።
4፤ ዩክሬን ወታደሮቿ ጣልቃ እየገቡ መሆኑን በመግለጽ የሩሲያ ጋዝ መተላለፊያን ዘጋች።ቁልፍ ነው የተባለለት ጋዝ መተላለፊያው ሩሲያ ለአውሮፓ ከምታቀርበው ነዳጅ ሶስት እጅ ያህሉ የሚተላለፍበት ነበር ተብሏል፡፡ ነዳጁን የማስተላለፍ ግዴታ ያለባት ዩክሬን በሌላ የማስተላለፊያ መስመር ለአውሮፓ አደርሳለሁ ብትልም እርምጃው በአውሮፓ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ንረት የበለጠ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡
ኪቭ የሶክራኒቭካ መተላለፊያን የዘጋችው አካባቢውን የተቆጣጠሩት የሩሲያ ወታደሮች ቴክኒካል በሆኑ ነዳጅ የማስተላለፍ ስራዎች ጣልቃ እየገቡ ነው በሚል ነው፡፡ ከረቡዕ ጀምሮ በሶክራኒቭካ በኩል ጋዝ ወደ አውሮፓ ማስተላለፉን እንደሚያቆምም የሃገሪቱ የጋዝ መተላፊያዎች አስተዳደር (GTSOU) አስታውቋል፡፡
5፤ማንችስተር ዩናይትድ የወጣቶቹን ኤፌ ካፕ አሸንፏል። በተመልካች ቁጥር አዲስ ታሪክን ያስመዘገበው የወጣቶቹ ( ከ 18ዓመት በታች ) የኤፌ ካፕ ፍፃሜ በማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል ። 67,492 ታዳሚያን በ ኦልድ ትራፎርድ ጨዋታውን ሲታደሙ አሊያንድሮ ጋራንቾ ሁለት ግቦች እና ቤኔት ኖቲንግሀም ፎረስትን የረቱበትን ጎሎች አስቆጥረዋል ። አሁን ላይ በአካዳሚው ጥሩ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው አሊያንድሮ ጋራንቾ በውድድሩ ላይ በአስር ጎሎች ላይ ተሳትፎን በማድረግ ቀዳሚውን ደረጃ ይይዛል ። ጨዋታውን የክለቡ የቀድሞ ታላላቅ ግለሰቦች ራያን ጊግስ እና ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ታድመውታል ።
• @ThinkAbyssinia •
8.8K views07:22