Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-09-24 10:25:00
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን  እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ዪፈልጋሉ ፤ እንግዲያውንስ ይሄን ሊንክ ይጫኑ፡፡ከላይ ያሉትን የጫማዎች ዋጋ እና ብዙ አማራጮችን ለማግኘት  ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ


https://t.me/joinchat/AAAAAElITjwlFLHHO8h7Sg


ይዘዙ በውስጥ መስመር የመረጡትን ፎቶ  ይላኩልን በቀላሉ እናስተናግዳለን ግዜዎን ቆጥበን።
inbox 1         inbox2
    @businesslidu   @businesslidu2

online shopping is always a good idea!!
አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ መ/ም ኤድናሞል አደባባይ ዞሮ ሬድዋን ህንጻ ጎን ራክሲም ህንጻ 3ኛ ፎቅ በስተቀኝ ዞር ሲሉ ያገኙናል።

0919998383
በውስጥ መስመር ለመፃፍ    @businesslidu & @businesslidu2
6.5K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 09:00:40
በመዲናዋ ከፊታችን እሁድ እስከ ማክሰኞ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወሰነ

እሁድ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17 ምሽት 12:00 ድረስ የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 17 ቀን የሚከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር መወሰኑን የአዲስ አበባ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

• @ThinkAbyssinia •
7.2K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:33:12
በእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

ዛሬ ሌሊት 7 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ቱሉዲምቱ አካባቢ የተለያዩ አነስተኛ የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ 15 የሚሆኑ በላስቲክ፣ በሸራና አነስተኛ ቁሳቁስ ተሰሩ መጠለያዎች በእሳት አደጋ መውደማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዕሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አምስት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከአደጋዉ ማዳን መቻሉን ገልፀው ይሁን አንጂ ከእነዚህ ሱቆች መካከል በመጽሀፍት ንግድ ላይ የሚሰራ እድሜው 32 ዓመት የሆነ ሰው በሱቁ ውስጥ እንደተኛ ህይወቱ ያለፈ መሆኑንና 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረትም መውደሙን ለፋና ተናግረዋል።

• @ThinkAbyssinia •
914 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:16:24
#ቲንክአቢሲኒያ_እለታዊ_የአየር_ትንበያ_መረጃ

ጤና ይስጥልን እንደምን አድራችኋል ውድ ቤተሰቦቻችን፤ እስቲ ለውሎዎ ጠቃሚ የሆኑ እለታዊ የአየር ትንበያ መረጃዎችን እናድርስዎ

ዛሬ በአንዳንድ የሀገራችን ከተሞች ያለውን ያየር ሁኔታ ስንመለከት መዲናችን አዲስ አበባ ዝቅተኛው 13 ከፍተኛው 23 ድግሪ ሲልሽየስ ቀላል ዝናብ ታስተናግዳለች።

ባህርዳር ዝቅተኛው 16 ከፍተኛው 25 ቀላል ዝናብ ሀዋሳ ዝቅተኛው 16 ከፍተኛው 24 ዝናባማ እንዲሁም መቀሌ ዝቅተኛው 11 ከፍተኛው 25 የአየር ሁኔታው ከፊል ደመናማ ሆነው እንደሚውሉ ቲንክአቢሲንያ ከቤሄራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ ድረገፅ ተመልክቷል።

ኤጀንሲው የዕለቱን የአየር ሁኔታ ትንበያ ባስቀመጠው መሠረት የሌሎቹን ከተሞች ዕለታዊ የሙቀት መጠን መረጃ በድግሪ ሴልሺየስ ከምስሉ ላይ ይመልከቱ።

         መልካም ቀን ይሁንልዎ
• @ThinkAbyssinia •
1.3K views05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:10:35
አርቲስት ሃሌሉያ ተክለፃድቅ የመጀመርያ የሆነውን የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች አቀረበች

የአልበሙ መጠሪያ "ተወዳጅ" የሚል ሲሆን ከመስከረም 13-2015 ጀምሮ በራሷ በአርቲስቷ ኦፊሴላዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የ ኢንተርኔት ሙዚቃ ማሰራጫዎች ሙዚቃው ይለቀቃል ተብሏል።

አርቲስቷ ታዋቂ ከሆነው ጃኖ ባንድ ጋር በሙዚቃ አጃቢነት በጋራ ስትሰራ የቆየች ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷ የፈጠራ ልጅ የሆነውን "ተወዳጅ" የተሰኘ አልበም ይዛ መጥታለች።

• @ThinkAbyssinia •
7.7K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 19:10:44 #ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት የዓለም አየር መንገድ ሽልማቶችን አሸነፈ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይትራክስ 2022 የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ አራት ሽልማቶችን አሸንፏል። በዚህም አየር መንገዱ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ የምጣኔ ሀብት ደረጃ አየር መንገድ እንዲሁም በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን አሸንፏል፡፡

2፤ከአፋር ክልል ህዝብ 75 በመቶው የምግብ እጥረት አለበት ተባለ።

75 በመቶ ያህሉ የአፋር ሕዝብን የምግብ እጥረት ያለበት ተብሎ መለየቱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤትን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት ዳግም ባገረሸው ጦርነት ሰለባ የሆኑ ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው በአራት መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል።

3፤ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ።

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዴቪድ ማካሊስተር የተመራውን ልዑክ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በአፍሪካ ሕብረት ስለሚመራው የሰላም ንግግር ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንዳመላከተው የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ከልዑኩ ጋር ተገኝተው በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

4፤ሩሲያ አውሮፓንና አሜሪካን በሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ልትመታ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

ለአዲሱ ተልዕኮዋ እንዲረዳትም 300 ሺህ ተጠባባቂ ጦሯን የጠራችው ሩሲያ ብሄራዊ ደህንነቷ ስጋት ውስጥ ከገባ ደግሞ የኑክሌር ጦሯን ጨምሮ ማንኛውንም መንገድ እንደምትጠቀም ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናግረዋል። ለዚህ ጉዞዋ እንቅፋት ከሆኑ አውሮፓን እና አሜሪካን በሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ልትመታ እንደምትችል አስጠንቅቃለች።

5፤ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ52 ብር ከ5646 ሳንቲም ሲገዛ ውሏል።

እንዲሁም መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ6159 ሳንቲም መሆኑን ከድረገጹ ተመልክተናል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋው 56 ብር ከ7402 ሳንቲም እንዲሁም መሸጫው 57 ብር ከ8750 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ51 ብር ከ2028 ሳንቲም እየተገዛ በ52 ብር ከ2269 ሳንቲም የተሸጠ ሲሆን፣ አንድ የቻይና ዩዋን ደግሞ በ6 ብር ከ7172 ሳንቲም ተገዝቶ በ6 ብር ከ8615 ሳንቲም ሲሸጥ እንደነበር ቲንክአቢሲኒያ ተመልክቷል።

6፤ቅዱስ ጊዪርጊስ በመለያያ ምት ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈ።

ዛሬ በ 16ተኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ለዋንጫ ለማለፍ በሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተገናኝተው ጨዋታው በመደበኛው 90 ደቂቃ 1 አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት ያመሩ ሲሆን በመጨረሻም በ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዋንጫው ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ለሁለቱም የመዲናዋ ክለቦች በድምሩ ሀያ ሚሊዮን ብር መስጠታቸውን ገልፀዋል።

• @ThinkAbyssinia •
8.1K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 17:28:32
የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺህ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የሸኔ አባል እንደሆነ የተጠረጠረው ግለሰቡ የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺ ብር ከሕጻኑ ወላጆች በመቀበል ልጁን ሆለታ ከተማ ጫካ ውስጥ ጥሎ መሄዱ ተገልጿል፡፡ ከዚያም ዘነበ ወርቅ መናኸሪያ በመሳፈር ወደ ጅማ ከተማ ሊያመልጥ ሲል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጅማ በር ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

• @ThinkAbyssinia •
2.5K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 16:19:20
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የደልሂ ግማሽ ማራቶን አምባሳደር ሆነ

የህንዱ የስፖርት መፅሄት የሆነው ዘ ሂንዱ እንዳስታወቀው የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው ኃይሌ ገብረሥላሴ በፈረንጆቹ ጥቅምት 16 ቀን በሚካሄደው የቬዳንታ ደልሂ ግማሽ ማራቶን አምባሳደር ሆኖ ተመርጧል፡፡

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በተለያዩ ውድድሮች 27 ጊዜ ክብረ ወሰን መስበር የቻለ ሲሆን ይህም በረጅም ርቀት የምንጊዜውም ምርጡ አትሌት ያደርገዋል ብሏል ዘገባው።

• @ThinkAbyssinia •
4.4K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 13:45:43
ሩሲያ ከዩክሬን በነጠቀቻቸዉ  አራት ግዛቶች ህዝበ ዉሳኔ ማካሄድ ጀመረች  

ህዝበ ዉሳኔዉ የሚካሄደዉ በ ሉሃንስክ፤ ዶኔስክ፤ በኬርሶንና በዛፖርዢያ ግዛቶች ሲሆን ሂደቱ እስከ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ድረስ  እንደሚቀጥልም የአገሪቱ መንግስት አስታዉቋል፡፡

ምዕራባዉያኑ ግን ህዝበ ዉሳኔዉን ለይስሙላ የሚደረግ ሲሉ አጣጥለዉታል፡፡ ሩሲያ ከስምንት አመት በፊት ከዩክሬ በወሰደችዉ ክረሚያ ግዛት ተመሳሳይ ህዝበ ዉሳኔ አድርጋ ማጠቃለሏ የሚታወስ ነዉ፡፡

• @ThinkAbyssinia •
6.6K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 12:02:49
ቦይንግ ተጨማሪ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል እያወቀ ዝም በማለቱ ተቀጣ

በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ከደረሱ አደጋዎች በኋላ ለባለሃብቶች የአደጋውን መንስኤ በመደበቁ 200 ሚሊዮን ዶላር  ሲቀጣ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የነበሩት ዴኒስ ሙሌንበርግም ሐቁን ባለመናገራቸው በግል 1 ሚሊዮን ዶላር መቀጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ይህን ያደረጉትም የቦይንግን ስምና ዝና ለመጠበቅ በሚል ነው ብሏል ዘገባው።  737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ ለ20 ወራት ያለ ሥራ እንዲቆሙ መደረጋቸው ይታወሳል።

• @ThinkAbyssinia •
7.7K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ