Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-09-27 15:38:19
#እጅግ_አሳዛኝ_ዜና
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ

ድምጻዊው ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል።


ድምፆዊ ማዲጎ አፈወርቅ እንደማንኛውም ድምፆዊ ዘመን የሚሻገር ስራ ባለቤት ነው::


ቲንክ አቢሲኒያ በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፡ ለአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።

• @ThinkAbyssinia •
7.7K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 14:46:28
#Update

የእሳት አደጋው በቁጥጥር ስር ውሏል

ቦሌ መስፍን ቁርጥ እና ጠጅ ቤት የተከሰተዉ የእሳት አደጋ በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ የከፋ አደጋ ሳያደርስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የአደጋው መንስዔ ከኩሽና አካባቢ የተነሳ ቃጠሎ መሆኑን የአደጋ መከላከል ሰራተኞች ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል። አደጋው በንብረት ላይ ብቻ የተከሰተ ሲሆን መጠኑ ገና እየተጣራ ይገኛል።

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •
8.0K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 13:08:28
#ለበአል_ጥንቃቄ

ቦሌ መስፍን ስጋ ቤት ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከሰተ

እሳቱ ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •
8.2K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 12:50:55
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል በዓልን  ምክንያት በማድረግ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው የምሳ ግብዣ አደረጉ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአሉን ምክንያት በማድረግ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው የሰራዊቱ አባላት በመጎብኘት  የተለያዩ ድጋፎችንና  የምሳ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ‹‹በእናንተ መሃል ተገኝቶ በዓልን ማሳለፍ  ከክብርም በላይ ክብር ነው፤ እናንተ የአገራችን ጀግኖች የአገራችን አርማ  ናችሁ"ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በገጠማት ፈተናዎች ሁሉ ፀንታ መሻገር እንድትችል ከስጦታ ሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ በመስጠት ሃገራችሁን ያፀናችሁ በመሆናችሁ ከእናንተ ጋር መሆን በእጅጉ ያስደስተናል  ሲሉም ጨምረዋል፡፡

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •
8.0K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 12:49:58
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን  እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ዪፈልጋሉ ፤ እንግዲያውንስ ይሄን ሊንክ ይጫኑ፡፡ከላይ ያሉትን የጫማዎች ዋጋ እና ብዙ አማራጮችን ለማግኘት  ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ


https://t.me/joinchat/AAAAAElITjwlFLHHO8h7Sg


ይዘዙ በውስጥ መስመር የመረጡትን ፎቶ  ይላኩልን በቀላሉ እናስተናግዳለን ግዜዎን ቆጥበን።
inbox 1         inbox2
    @businesslidu   @businesslidu2

online shopping is always a good idea!!
አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ መ/ም ኤድናሞል አደባባይ ዞሮ ሬድዋን ህንጻ ጎን ራክሲም ህንጻ 3ኛ ፎቅ በስተቀኝ ዞር ሲሉ ያገኙናል።

0919998383
በውስጥ መስመር ለመፃፍ    @businesslidu & @businesslidu2
6.9K views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 10:29:41 #ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የመስቀል በዓል በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በተለይም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ምዕመናን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ነው በድምቀት የተከበረው።

2፤ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች "ባለሙያዎች" ቡድን እንዲፈርስ ጥያቄ ቀረበ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀት አባላት ጥምረት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይን እንዲመረምር የተሰየመው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች "ባለሙያዎች" ቡድን እንዲፈርስ ጥያቄያቸውን ለተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነርና ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክር ቤት አባል ሀገራት አቅርበዋል። ጥምረቱ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ቡድን በፈረንጆቹ መስከረም 22፣ 2022 ባወጣው ሪፖርት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለማቅረብ በጻፉት ደብዳቤ አማካኝነት መሆኑም ታውቋል።

3፤ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።

ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በኡሙሩ፣ ሆሮ ቡልቅ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ኢመደበኛ ታጣቂዎች ከነሐሴ 25 ጀምሮ ባሉት ሦስት ሳምንታት ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች ገድለዋል ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ የፌደራል እና ክልል ባለሥልጣናት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸም ብሄርን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንዲያስቆሙም ጠይቋል።

4፤መረጃ አሳልፎ ሰጥቷል ስትል አሜሪካ በጥብቅ ለምትፈልገው ሰው ሩሲያ ዜግነት ሰጠች።

የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ለቀድሞ የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ሰራተኛ እና መረጃ አሳልፎ ለሰጠው ኤድዋርድ ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት እንዲሰጠው በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡ ስኖውደን በፈንጆቹ 2013 የአሜረካ መንግስት የጀርመኗን መሪ ጨምሮ የ35 ሀገራት መሪዎችን ስልክ እና ኢሜል ላይ ስለላ ማድረጓን አጋልጦ ነበር፡፡ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት ከተሰጣቸው 70 የውጭ ሀገራት ዜጎች መካከል አንዱ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

5፤የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ-ግብር ማሻሻያ ተደረገበት።

የፊታችን ዓርብ የሚጀምረው የመጀመሪያ ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ-ግብር ማሻሻያ ተደረገበት። የመርሃ ግብር ማሻሻያው በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ላይ ስለሚሳተፍ የፋሲልን ጨዋታዎች ታሣቢ በማድረግ የሊጉ የበላይ አካል የጨዋታ ፕሮግራም ማስተካከያ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •
7.3K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 10:28:12
ኪያድ ዳቦ እና ኬክ
Kiyad Bakery and Coffee

ለልደት፣ ለሰርግ እና ለምርቃት በፈለጉት ዲዛይን እና መጠን እናዘጋጃለን።

Bring us your cake designs! We prepare cakes for every occasion!

0911467026
0913911679

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

https://t.me/kiyad_bakery

አድራሻ: ልደታ ፍሊንት ስቶን አካባቢ
      የልደታ የፍታብሔር ምድብ ችሎት ፊት ለፊት

https://maps.app.goo.gl/4hYtermcawkxksDH7
6.9K viewsedited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 08:04:40
ደመራ በዋሽንግተን ዲሲ(አሜሪካ)

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያውያን የመስቀል በዓልን በደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ማክበራቸውን ዋሽንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታዉቋል።

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •
7.6K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 07:30:22
ጀግኖቹ ከ30 ዓመት በኋላ ዳግም ተገናኙ

እኤአ በ1992 የባርሴሎና ኦሊምፒክ በ10ሺ ሜትር ውድድር ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የወርቅና የብር ሜዳልያ ያስገኙት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ እና ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤሊና ማየር ዳግም በባርሴሎና ተገናኝተዋል።

የቀድሞው አትሌቶቹ የተገናኙት የባርሴሎና ኦሎምፒክ 30ኛ አመትን ለመዘከር በባርሴሎና በተሚካሄደው ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ተጋብዘው ነው።

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
• @ThinkAbyssinia •
7.5K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 07:19:33
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ

በአሉ የሠላም፤ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንላቹ ቲንክአቢሲኒያ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •
7.7K viewsedited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ