Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-10-05 15:05:26
አገር የሚገቡ የግል ዕቃዎችን በሚገድበው መመርያ ምክንያት በርካታ ንብረቶች በጉምሩክ መያዛቸው ተገለጸ

ከአንድ ወር በፊት በገንዘብ ሚኒስቴር ፀድቆ ተግባራዊ የሆነው የግል መገልገያ ዕቃዎች በቁጥር ከሚገድበው አዲሱ መመርያ፣ የቀረጥ ታክስ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር የሚገቡና ከአገር የሚወጡ ዕቃዎች ላይ የቁጥር ገደብ በማውጣት የሚወስን ሲሆን፣ ማንኛውም መንገደኛ ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ አገር ማስገባት የሚችላቸውን የ16 ዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር አውጥቷል።

በዝርዝር በመመርያው የተጠቀሱት ዕቃዎችና ሌሎችም ያልተጠቀሱ ንብረቶችን ተጓዦች እንደ ከዚህ ቀደሙ ወደ አገር ይዘው ሲገቡ ንብረቱን ከገዙበት በላይ ከፍተኛ ቀረጥ እየተጠየቁ በመሆኑ፣ ይህም ከፍተኛ ብዥታ እየፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በርካቶች ለመክፈል ባለመቻላቸውና ባለመፈለጋቸውም እዚያው ንብረቶቻቸውን ትተውት እየወጡ እንደሆነና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በአየር ማረፊያው ያሉት መጋዘኖች ቀረጥ ሳይከፈልባቸው እዚያው በቀሩ በርካታ እቃዎች እያጨናነቁ እንዳሉ ሪፖርተር ዘግቧል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ ግለሰብ ከአንድ ሳምንት በፊት ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ 55 ኢንች ሰምሰንግ ቴሌቪዥን ይዞ ወደ አዲስ አበባ የመጣ ሪፖርተር ያነጋገረው አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ግለሰብ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ በአዲሱ መመርያ መሠረት ቀረጥ ከፍሎ ማስገባት እንዳለበት ቢረዳም፣ እንዲከፍል የተጠየቀው ገንዘብ ግን እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ንብረቱን እዚያው ትቶት እንደሄደ ይገልጻል። ቴሌቪዥኑ በዱባይ የሚያወጣው ዋጋ ከ1,500 ድራም (19,500 ብር) እንደማይበጥና እሱ ግን የዋጋውን ሦስት እጥፍ በአጠቃላይ ከ65,000 ሺሕ ብር የበለጠ እንዲከፍል መጠየቁን ለሪፖርተር ተናግሯል።

• @ThinkAbyssinia •
10.3K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 11:28:19
አሜራካ በኢትዮጵያ የሚመረተው ዊስኪ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ፈቀደች።

በኢትዮጵያ የሚመረተውን “ብላክ ዲር ዊስኪ” በአሜሪካ ገበያዎች ለማስተዋወቅ ከአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) ፈቃድ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ አስታውቀዋል ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

ሰሞኑን በአሜሪካን ዋሽግንተን ዲሲ በተካሄደውና በሀገራችን ኢትዮጵያ እና ተቀማጭነታቸውን አሜሪካን ሀገር ያደረጉ የተለያዩ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የምግብ፤ የመጠጥና የባህል ፌስቲቫል ላይ የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ አዲሱን ብላክ ዲር ዊስኪን ጨምሮ ተወዳጅ ምርቶቹን በፌስቲቫሉ ላይ አስተዋውቋል፡፡

የፋብሪካው ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል "አሜሪካ የመጣነው ምርቱን ለኢትዮጵያዊያን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲገባ ትልቅ ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።

የፋብሪካው ዓመታዊ ገቢ 300 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንና ባለፈው ዓመት ብቻ ወደ አንድ ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገኘቱን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከተቋቋመ ከ116 ዓመታት በላይ እንደሆነው ተገልጿል።

via - VOA
• @ThinkAbyssinia •
10.3K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 09:01:47
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች።

አንድ መቶ ዘጠና ሶስት ሀገራትን በአባልነት የያዘው የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በካናዳ ሞንትሪያል ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያን በመወከልም የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ተሳትፈዋል። በዚህ ጉባኤም ኢትዮጵያ የድርጅቱ ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊ ገልፀዋል።

via - fbc
• @ThinkAbyssinia •
2.0K views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 07:35:17 ኑሮ ለምን ተወደደ

ሞያዊ ምልከታዎች መንግስትንም ተጠያቂ የሚያደርጉ ናቸው የሚሉት አስተያየታቸው ለባላገሩ ቲቪ የሰጡ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች መንግሥት የዋጋ ንረትን የሚያባብሱ እርምጃዎች ከመውሰድ መቆጠብ እንዳለበት አሳስበዋል። በልቶ ማደር ከበደን የሚል እሮሮ የሚያሰማው የማኅበረሰብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ ከሰሞኑ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃኑ ላይ ሲዘዋወር የቆየው መብላት የቸገራቸው እናት መሶባቸው ለመሸጥ አደባባይ መውጣት ለዚህ ላነሳነው ጉዳይ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

የምርቶች ዋጋ በየዕለቱ ለእጥፍ በተጠጋ ዋጋ እየጨመረ ይገኛል። የምርቶች ዋጋ በቀናት ብቻ ሳይሆን በሰዓታት ልዩነት  የሚለዋወጥበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል፡፡ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ የዋጋ ንረት መታየት እንደ ጀመረ የጥናት ውጤቶች ያሳያሉ፤ የዋጋ ንረቱ ባለፉት ዐሥርት ዓመታት የሚያቆመው ልጎም አጥቶ ለብዙ ሕዝብ የጭንቀት ምክንያትም ሆኗል፡፡

መንግሥት የዋጋ ንረቱን ያረጋጋል ያላቸውን በርካታ እርምጃዎች እየወሰደ እንደሆነ ቢናገርም እስካሁን በመሬት ላይ የተቀየረ ነገር እንደሌለ የማእከላዊ ስታስቲክ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣውን የዋጋ ግሽበት ቁጥራዊ መረጃ መመልከት ይቻላል።

የመንግስት እርምጃዎች እና አንድምታቸው

"መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች የዋጋ ንረቱን እያባባሰው ነው" ይላሉ የምጣኔ ኃብት ባለሞያዎችም። መንግሥት ባለፉት ዓመታት የነዳጅ ፣የመዘጋጃ ቤት አገልግሎት ፣ የኤሌትሪክ ታሪፍ ላይ ጭማሪ ማድረጉ የዋጋ ንረቱን በተወሰነ መልኩ እንዳባበሰው ያነሳሉ፡፡

* የነዳጅ እና መሰል የዋጋ ጭማሬዎች

ከሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ የዋጋ ንረት  ላይ የራሱን ጫና መፍጠሩን ያነሱት የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ዶ/ር አስፋው አድማሴ ናቸው፡፡ መንግሥት በአንድ ጊዜ የተጋነኑ የሚመስሉ የዋጋ ጭማሪዎችን ከማድረግ ይልቅ በሂደት የሚጨምርበት ሁናቴ ቢፈጠር ይተሻለ እንደሆነም  የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ይመክራሉ፡፡

* በቃል የቀሩ ውሳኔዎች

ሌላኛው ለባላገሩ አስተያየታቸውን የሰጡት የምጣኔ ኃብት ባለሞያው አቶ አጥላው አለሙ  ናቸው፡፡ መንግሥት ከኢኮኖሚው ጋር በተያያዘ የሚሰጣቸው አስተያየቶች እና መሬት ላይ የሚታየው እውነታ የተለያየ መሆኑ ኢኮኖሚው ተገማች እንዳይሆን ፤ ነጋዴው እና ሸማቹ በመንግሥትም እምነት እንዳይጣልበት አድርጎል ይላሉ፡፡

መንግሥት ቀድሞ መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሳይወስድ በመቆየቱ የዋጋ ውድነቱ  ዛሬ የደረስንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል የሚሉት ዶ/ር አስፋው ተበላሽተው የቆዩ የገበያ ስርዓቶች ሳይጠገኑ በመቆየታቸው የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰው አንስተዋል፡፡

* ፍራንኮ ቫሎታ

"ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዶላር አንፃር የብር የመግዛት አቅም እያደከመ መጥቷል። ይህም 80 በመቶ በላይ ምርቷን ከውጭ ለምታስገባ አገር የምርት ዋጋ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል" የሚሉት የምጣኔ ኃብት ባለሞያው በቅርቡ የተፈቀደው 'የፍራንኮ ቫሉታ )'/አሰራር በትይዩ ገበያ ( በጥቁር ገበያ ) እና በባንኮች የምንዛሬ ዋጋ ላይ ሰፊ ክፍተት መፍጠሩን ያነሳሉ ይህም የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰው ጠቁመዋል፡፡

* የአዳዲስ ገንዘብ ህትመት

ሌላኛው ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ዋነኛ ምክንያት መንግሥት አትሞ ወደ ገበያው የሚለቀውን የገንዘብ መጠን መጨመሩ እንደሆነ የሚያነሱት ዶ/ር አጥላው በገበያው ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መብዛት ገንዘብ የመግዛት አቅሙ እንዲዳከም አድርጎታል ባይ ናቸው። ይህም ሁሉም ምርት በአንድ ጊዜ  እንዲጨምር ማስገደዱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

* ቅድሚ የሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች አለመለየት

ባለፉት ዓመታት መንግሥት በብድር እና እርዳታ የሚያገኛቸውን ገንዘቦች ፈጣን ተመላሽ በሌላቸው ፕሮጀክቶች ላይ ሲያውል እንደነበረም ዶ/ር አጥላው ያነሳሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች በርካታ የሥራ እድል መፍጠር በማይችሉ፣ የምርት ውጤት በሌላቸው፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት አስተዋፅዖ የሌላቸው መሆናቸውን በማንሳት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የማይገባው መሆኑን ያሰምሩበታል፡፡

ምን አልባት ይህ ገንዘብ በሌሎች ምርትቶች እና ውጤት ባላቸው ሥራዎች ላይ ቢያርፉ የተሻለ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡መንግሥት የዋጋ ንረቱን የሚያባብሱ እርምጃዎችን ከመውሰድ መቆጠብ እንዳለበት የሚያነሱት ባለሞያዎቹ በተቻለ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

via - ባላገሩ ቴሌቪዥን
• @ThinkAbyssinia •
3.8K views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 07:33:42
3.7K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 18:06:54
ሚኒስትሩ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ።

መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ቀጠናው ትስስር ሚኒስቴር አሰታውቋል።

የንግድና ቀጠናው ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሠረታዊ ሸቀጦች እና መሰል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ ተሳትፊ የሆኑ አካላት ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ በማስጠንቀቅ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በህገ-ወጥ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡

በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልል  ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መሰል እርምጃዎችን እንደሚወስድ በመጠቆም ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም እንደነዚህ ያሉ ህገ ወጥ አካላትን ሲያስተውል ለሚመለከታቸው የንግድ ቢሮ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

• @ThinkAbyssinia •
6.2K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 17:10:29
በመዲናዋ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ22 ሺ በላይ ኩንታል ሲሚንቶ መያዙ ተነገረ።

ተግባራዊ የተደረገው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ከሚፈቅደው ውጪ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 22 ሺህ 293 ኩንታል ሲሚንቶ ተይዞ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ከዚህ ውስጥም 15 ሺህ 179 ኩንታሉ ተወርሶ መሸጡንም ተገልጿል።

በተጨማሪም 2 ሺህ 226 ኩንታሉ ተጣርቶ ህጋዊነቱን የሚያረጋግጡ መረጃዎች ተሟልተው ሲለቀቅ፥ ቀሪው መንግስት በተመነው ዋጋ መሸጡ ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮም ለከተማው የተመደበው ሲሚንቶ ከተቀመጠው አሰራር ውጭ ግብይት ላይ እንዳይውል ከኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ መግቢያ በሮች ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

via - EBC
• @ThinkAbyssinia •
6.6K views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 14:27:03
ቱርክ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ ተነገረ።

በቱርክ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለለት የዋጋ ግሽበት እንደተከሰተ ቢቢሲ ፅፏል። በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሸበት 83 በመቶ መድረሱ ሲገለፅ ትራንስፖርት፣  ምግብ እና የቤት ዘርፎች ደግሞ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ኢንፍሌሽን ሪሰርች ግሩፕ የሚባለው ገለልተኛ የአጥኚዎች ቡድን ዓመታዊውን የዋጋ ግሽበት 186.7 በመቶ ደርሷል ማለቱን ዘገባው አክሏል።

ባለፈው ዓመት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በሚል ባልተለመደ ሁኔታ የወለድ ምጣኔውን ቀንሰው ነበር። በርካታ ባንኮች ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል የወለድ መጠናቸውን ከፍ አድርገው ነበር። በዚህም የተነሳ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሊራን ዋጋ የቀነሰው ሲሆን አገሪቱም ከውጭ የምታስገባቸው ዕቃዎችን በከፍተኛ ዋጋ እንድትገዛ ተገዳለች። ሊራ ከዶላር አንጻር ያለው ልዩነት ክብረወሰን በሆነ ደረጃ ቀንሶ 1 የኤሜሪካ ዶላር በ18.56 ሊራ እየተመነዘረ ነው።

የአሜሪካው ባንክ ጂፒ ሞርጋን የቱርክ የዋጋ ግሽበት “የፖሊሲ ለውጥ ካልተደረገ ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ይሆናል ብሏል። ሰኞ ምሽት በቴሌቭዥን ፊት የቀረቡት ፕሬዝዳንት አርዶሃን በበኩላቸው “ይህንን የዋጋ ግሽበት ችግር አራግፈን በጋራ ጠንካራዋን ቱርክ እንገነባለን” ብለዋል።

via - BBC
• @ThinkAbyssinia •
8.0K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 12:05:20
ዲቪ 2024 ነገ ይጀምራል።

ዲቪ 2024 ከረቡዕ መስከረም 25  እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም (በፈረንጅ አቆጣጠር ከኦክቶበር 5 እስከ ኖቬምበር 8/2022) በኦንላይን ማመልከት እንደሚቻል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ አድርጓል።

ለማመልከት

ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅ ግድ ይላል፣

ማመልከት የሚቻለው በኦንላይን ብቻ ሲሆን ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣

በኦንላይን ከሞሉ በኋላ የሚደርስዎ የማረጋገጫ ቁጥር ይያዙ። ዕጣው በሚወጣበት ወቅት በኦንላይን መመልከት የሚችሉት በዚሁ ቁጥርዎ ብቻ ነው፣

ከስድስት ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ መጠቀም ያስፈልጋል፣

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ሎተሪ ወይም ዲቪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ትወስዳለች። ከዚህ ውስጥ የአፍሪካ ድርሻ 38 ሺህ ነው።

• @ThinkAbyssinia •
8.9K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 11:05:46
የአማራ ክልል አንድ ሚሊዮን የቀን ሰራተኛ እፈልጋለሁ ማለቱ ተሰማ።

የአማራ ክልል አካል የሆነው የምዕራብ ጎንደር ዞን በዚህ የመህር ወቅት 6.9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ወደ አንድ ሚሊዮን የቀን ሰራተኞችን እፈልጋለሁ ማለቱ ተሰምቷል።  ዞኑ ይህ ጥሪ ያቀረበው በትግራይና በወሎ በተከሰተው ጦርነት ሰራተኞችን ለመቅጠር ስለተቸገረ መሆኑን ሪፖርተር ፅፏል።

ቢያንስ 20 ቀናት ሊወስድ ይችላል በተባለው በዚህ ስራ ከአምስት ቢሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ተመድቧል። የቀን ሰራተኞቹ እንደየስራው አይነት ከ250 ብር እስከ 300 ብር የሚከፈላቸው ሲሆን ለሰራተኞች ማረፊያ የሚሆን ካምፕም ተዘጋጅቷል፤ ድንገተኛ አደጋ ቢከሰት እንኳ የህክምና አገልግሎት ተሟልቷል የተባለ ሲሆን በዞኑም ከፌዴራል እና ከክልል የጸጥታ አካላት እና ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

የቀን ሰራተኞቹ በሰሊጥ፣ በሶያ ቦሎቄ እና በአረንጓዴ ሙግ ባቄላ በተሸፈነው 438,000 ሄክታር መሬት ላይ የተዘራውን ሰብል ይሰበስባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምዕራብ ጎንደር የኢትዮጵያ ዋና የቅባት እህሎች ቀበቶ በመሆን የሚታወቀው እንደ ቋራ፣መተማ ዮሃንስ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

በተያያዘም በዚህ አመት ተጨማሪ ምርት እንደሚጠበቅ የዞኑ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በ2021 የመኸር ወቅት ከ130,945 ሄክታር መሬት 930,000 ኩንታል የቅባት እህል መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መረጃ የሚጠቁም ሲሆን በዚህ አመት አሃዙ በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

• @ThinkAbyssinia •
8.6K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ