Get Mystery Box with random crypto!

ሚኒስትሩ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነ | Think Abyssinia

ሚኒስትሩ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ።

መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ቀጠናው ትስስር ሚኒስቴር አሰታውቋል።

የንግድና ቀጠናው ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሠረታዊ ሸቀጦች እና መሰል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ ተሳትፊ የሆኑ አካላት ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ በማስጠንቀቅ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በህገ-ወጥ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡

በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልል  ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መሰል እርምጃዎችን እንደሚወስድ በመጠቆም ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም እንደነዚህ ያሉ ህገ ወጥ አካላትን ሲያስተውል ለሚመለከታቸው የንግድ ቢሮ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

• @ThinkAbyssinia •