Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ22 ሺ በላይ ኩንታል ሲሚንቶ መያዙ ተነገረ። ተ | Think Abyssinia

በመዲናዋ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ22 ሺ በላይ ኩንታል ሲሚንቶ መያዙ ተነገረ።

ተግባራዊ የተደረገው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ከሚፈቅደው ውጪ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 22 ሺህ 293 ኩንታል ሲሚንቶ ተይዞ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ከዚህ ውስጥም 15 ሺህ 179 ኩንታሉ ተወርሶ መሸጡንም ተገልጿል።

በተጨማሪም 2 ሺህ 226 ኩንታሉ ተጣርቶ ህጋዊነቱን የሚያረጋግጡ መረጃዎች ተሟልተው ሲለቀቅ፥ ቀሪው መንግስት በተመነው ዋጋ መሸጡ ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮም ለከተማው የተመደበው ሲሚንቶ ከተቀመጠው አሰራር ውጭ ግብይት ላይ እንዳይውል ከኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ መግቢያ በሮች ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

via - EBC
• @ThinkAbyssinia •