Get Mystery Box with random crypto!

በቱርክ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ ተነገረ። በቱርክ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ከፍተ | Think Abyssinia

ቱርክ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ ተነገረ።

በቱርክ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለለት የዋጋ ግሽበት እንደተከሰተ ቢቢሲ ፅፏል። በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሸበት 83 በመቶ መድረሱ ሲገለፅ ትራንስፖርት፣  ምግብ እና የቤት ዘርፎች ደግሞ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ኢንፍሌሽን ሪሰርች ግሩፕ የሚባለው ገለልተኛ የአጥኚዎች ቡድን ዓመታዊውን የዋጋ ግሽበት 186.7 በመቶ ደርሷል ማለቱን ዘገባው አክሏል።

ባለፈው ዓመት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በሚል ባልተለመደ ሁኔታ የወለድ ምጣኔውን ቀንሰው ነበር። በርካታ ባንኮች ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል የወለድ መጠናቸውን ከፍ አድርገው ነበር። በዚህም የተነሳ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሊራን ዋጋ የቀነሰው ሲሆን አገሪቱም ከውጭ የምታስገባቸው ዕቃዎችን በከፍተኛ ዋጋ እንድትገዛ ተገዳለች። ሊራ ከዶላር አንጻር ያለው ልዩነት ክብረወሰን በሆነ ደረጃ ቀንሶ 1 የኤሜሪካ ዶላር በ18.56 ሊራ እየተመነዘረ ነው።

የአሜሪካው ባንክ ጂፒ ሞርጋን የቱርክ የዋጋ ግሽበት “የፖሊሲ ለውጥ ካልተደረገ ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ይሆናል ብሏል። ሰኞ ምሽት በቴሌቭዥን ፊት የቀረቡት ፕሬዝዳንት አርዶሃን በበኩላቸው “ይህንን የዋጋ ግሽበት ችግር አራግፈን በጋራ ጠንካራዋን ቱርክ እንገነባለን” ብለዋል።

via - BBC
• @ThinkAbyssinia •