Get Mystery Box with random crypto!

አሜራካ በኢትዮጵያ የሚመረተው ዊስኪ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ፈቀደች። በኢትዮጵያ የሚመረተውን | Think Abyssinia

አሜራካ በኢትዮጵያ የሚመረተው ዊስኪ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ፈቀደች።

በኢትዮጵያ የሚመረተውን “ብላክ ዲር ዊስኪ” በአሜሪካ ገበያዎች ለማስተዋወቅ ከአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) ፈቃድ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ አስታውቀዋል ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

ሰሞኑን በአሜሪካን ዋሽግንተን ዲሲ በተካሄደውና በሀገራችን ኢትዮጵያ እና ተቀማጭነታቸውን አሜሪካን ሀገር ያደረጉ የተለያዩ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የምግብ፤ የመጠጥና የባህል ፌስቲቫል ላይ የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ አዲሱን ብላክ ዲር ዊስኪን ጨምሮ ተወዳጅ ምርቶቹን በፌስቲቫሉ ላይ አስተዋውቋል፡፡

የፋብሪካው ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል "አሜሪካ የመጣነው ምርቱን ለኢትዮጵያዊያን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲገባ ትልቅ ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።

የፋብሪካው ዓመታዊ ገቢ 300 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንና ባለፈው ዓመት ብቻ ወደ አንድ ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገኘቱን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከተቋቋመ ከ116 ዓመታት በላይ እንደሆነው ተገልጿል።

via - VOA
• @ThinkAbyssinia •