Get Mystery Box with random crypto!

አገር የሚገቡ የግል ዕቃዎችን በሚገድበው መመርያ ምክንያት በርካታ ንብረቶች በጉምሩክ መያዛቸው ተገ | Think Abyssinia

አገር የሚገቡ የግል ዕቃዎችን በሚገድበው መመርያ ምክንያት በርካታ ንብረቶች በጉምሩክ መያዛቸው ተገለጸ

ከአንድ ወር በፊት በገንዘብ ሚኒስቴር ፀድቆ ተግባራዊ የሆነው የግል መገልገያ ዕቃዎች በቁጥር ከሚገድበው አዲሱ መመርያ፣ የቀረጥ ታክስ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር የሚገቡና ከአገር የሚወጡ ዕቃዎች ላይ የቁጥር ገደብ በማውጣት የሚወስን ሲሆን፣ ማንኛውም መንገደኛ ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ አገር ማስገባት የሚችላቸውን የ16 ዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር አውጥቷል።

በዝርዝር በመመርያው የተጠቀሱት ዕቃዎችና ሌሎችም ያልተጠቀሱ ንብረቶችን ተጓዦች እንደ ከዚህ ቀደሙ ወደ አገር ይዘው ሲገቡ ንብረቱን ከገዙበት በላይ ከፍተኛ ቀረጥ እየተጠየቁ በመሆኑ፣ ይህም ከፍተኛ ብዥታ እየፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በርካቶች ለመክፈል ባለመቻላቸውና ባለመፈለጋቸውም እዚያው ንብረቶቻቸውን ትተውት እየወጡ እንደሆነና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በአየር ማረፊያው ያሉት መጋዘኖች ቀረጥ ሳይከፈልባቸው እዚያው በቀሩ በርካታ እቃዎች እያጨናነቁ እንዳሉ ሪፖርተር ዘግቧል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ ግለሰብ ከአንድ ሳምንት በፊት ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ 55 ኢንች ሰምሰንግ ቴሌቪዥን ይዞ ወደ አዲስ አበባ የመጣ ሪፖርተር ያነጋገረው አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ግለሰብ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ በአዲሱ መመርያ መሠረት ቀረጥ ከፍሎ ማስገባት እንዳለበት ቢረዳም፣ እንዲከፍል የተጠየቀው ገንዘብ ግን እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ንብረቱን እዚያው ትቶት እንደሄደ ይገልጻል። ቴሌቪዥኑ በዱባይ የሚያወጣው ዋጋ ከ1,500 ድራም (19,500 ብር) እንደማይበጥና እሱ ግን የዋጋውን ሦስት እጥፍ በአጠቃላይ ከ65,000 ሺሕ ብር የበለጠ እንዲከፍል መጠየቁን ለሪፖርተር ተናግሯል።

• @ThinkAbyssinia •