Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ንግድ መጠን በእጅጉ እንደሚቀንስ የዓለም ንግድ ድርጅት በትንበያው አመለከተ። የዓለም ን | Think Abyssinia

የዓለም ንግድ መጠን በእጅጉ እንደሚቀንስ የዓለም ንግድ ድርጅት በትንበያው አመለከተ።

የዓለም ንግድ ድርጅት የዓለም ኢኮኖሚ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ በ2023 የሚኖረው የዓለም ንግድ መጠን በእጅጉ እንደሚቀንስ በትንበያው አመላክቷል፡፡ የድርጅቱ ኢኮኖሚስቶች ጥናት እንደሚያመለክተው፤ በዚህ አመት የንግድ መጠኑ በ3 ነጥብ 5 በመቶ የሚያድግ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከተጠበቀው ትንሽ ከፍ ያለ ነው ተብሏል። ጥናቱ በ2023 የሚኖረው ዓለም አቀፍ የንግድ መጠን በአንድ በመቶ ብቻ እንደሚገደብና ይህም በሚያዝያ ወር ከነበረው የ3.4 በመቶ ትንበያ በእጅጉ እንደሚቀንስ አመላክቷል፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ በቅረቡ በጄኔቫ በተካሄደው ዓለም አቀፉ የንግድ ፎረም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር “ወደ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ድቀት ከመግባታችን በፊት ስለ ማገገም ማሰብ መጀመር አለብን ፤እድገትን መመለስ አለብን” ሲሉ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡

via - Al ain
• @ThinkAbyssinia •