Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ የቴሌኮም አገልግሎት በይፋ አስጀመረ። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስ | Think Abyssinia

ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ የቴሌኮም አገልግሎት በይፋ አስጀመረ።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሳኡሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣  ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ በርካታ ቅድመ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሳፋሪኮም ትልቅ ሚና ይኖረዋል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፣ ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር በጋራ በመስራት በሁሉም ቦታ ተደራሽ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል። የሳፋሪኮም ቴሌኮምኒኬሽን ኢትዮጵያ ምርቃት ስነስርዓት ላይ ለመታደም የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶም  አዲስ አበባ መግባታቸው ተሰምቷል።

ሳፋሪኮም ለደረሰበት ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮ ቴሌኮም እገዛ ትልቅ መሆኑን በመግልጽ አመስግነዋል።  ኩባንያው ባለፉት ሳምንታት በድሬዳዋ፣ በባህርዳር፣ በአወዳይ፣ ጎንደር ፣ሞጆ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ሀረር፣ ቢሾፍቱና ደብረ ብርሃን የኔትዎርክ ሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩ ይታወሳል።

via - ENA
• @ThinkAbyssinia •