Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁለት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማካሄድ ስም | Think Abyssinia

በመዲናዋ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁለት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት ተፈረመ

የመጀመሪያው ከ6 ነጥብ 1ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት ፕሮጀክትና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የሚገነቡ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ግንባታ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በመዲናዋ አስተማማኝ የግብርና ምርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያግዝና ገበያውን በማረጋጋት ለአምራቹ እና ለሸማቹ ተመጣጣኝ ምርቶች እንዲቀርቡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁለተኛው በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በሆነ ወጪ የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግ በተያዘው ቁርጠኝነት የሚገነባው የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ የB+G+8 ፕሮጀክት ግንባታ መሆኑ ተመላክቷል። ፕሮጀክቶቹ ኦቪድ ግሩፕ እና በተስፋዬ ኃይሌ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ይገነባሉም ተብሏል። የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በታቀደው ጊዜ ገደብ በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ ከንቲባ አዳነች አሳስበዋል።

via - mayor office of Addis Ababa 
• @ThinkAbyssinia •