Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የእንቁላል የነፍስ ወከፍ ፍጆታ በዓመት 7 እንቁላል ነው ተባለ፡፡ የኢትዮጵያውያን ዓ | Think Abyssinia

የኢትዮጵያ የእንቁላል የነፍስ ወከፍ ፍጆታ በዓመት 7 እንቁላል ነው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የእንቁላል የነፍስ ወከፍ ፍጆታቸው ሰባት እንቁላሎች ብቻ መሆኑ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው ጥናት አመላከተ። ከአፍሪካ አማካኝ ዓመታዊ የእንቁላል ፍጆታ አንፃር ሲታይም በ37 እንቁላሎች እንደሚያንስ ተጠቁሟል፡፡ የዶሮ ስጋ ፍጆታም በዓመት አንድ ኪሎ እንኳን ሳይሞላ 0.8 ኪ.ግ ብቻ መሆኑም ታውቋል።

በኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት ከ15 እስከ 17 በመቶ ድርሻ እንዳለው ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ቁጥርም በአፍሪካ አንደኛ እንዲሁም በዓለም ሰባተኛ ደረጃን የያዘች አገር ነች፡፡ አገሪቱ እምቅ የእንስሳት ሃብት ቢኖራትም ዜጎቿ በዓመት ማግኘት የሚገባቸውን የእንስሳት ተዋፅዖ እያገኙ አንዳልሆነ የተደረጉ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

የአገሪቱ የወተት ዓመታዊ የፍጆታ መጠን በዓመት 70 ሊትር ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት የአንድ ሰው ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ወደ 2 መቶ ሊትር ከፍ ማለት እንዳለበት ይመክራል፡፡ በእንስሳት ተዋፅዖዎች ላይ የሚታየው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ዜጎች ምረቶቹን ይበልጥ እንዳይጠቀሙ ማድረጉን የህብሩት ስራ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡

via - ባላገሩ ቲቪ
• @ThinkAbyssinia •