Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል አንድ ሚሊዮን የቀን ሰራተኛ እፈልጋለሁ ማለቱ ተሰማ። የአማራ ክልል አካል የሆነው | Think Abyssinia

የአማራ ክልል አንድ ሚሊዮን የቀን ሰራተኛ እፈልጋለሁ ማለቱ ተሰማ።

የአማራ ክልል አካል የሆነው የምዕራብ ጎንደር ዞን በዚህ የመህር ወቅት 6.9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ወደ አንድ ሚሊዮን የቀን ሰራተኞችን እፈልጋለሁ ማለቱ ተሰምቷል።  ዞኑ ይህ ጥሪ ያቀረበው በትግራይና በወሎ በተከሰተው ጦርነት ሰራተኞችን ለመቅጠር ስለተቸገረ መሆኑን ሪፖርተር ፅፏል።

ቢያንስ 20 ቀናት ሊወስድ ይችላል በተባለው በዚህ ስራ ከአምስት ቢሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ተመድቧል። የቀን ሰራተኞቹ እንደየስራው አይነት ከ250 ብር እስከ 300 ብር የሚከፈላቸው ሲሆን ለሰራተኞች ማረፊያ የሚሆን ካምፕም ተዘጋጅቷል፤ ድንገተኛ አደጋ ቢከሰት እንኳ የህክምና አገልግሎት ተሟልቷል የተባለ ሲሆን በዞኑም ከፌዴራል እና ከክልል የጸጥታ አካላት እና ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

የቀን ሰራተኞቹ በሰሊጥ፣ በሶያ ቦሎቄ እና በአረንጓዴ ሙግ ባቄላ በተሸፈነው 438,000 ሄክታር መሬት ላይ የተዘራውን ሰብል ይሰበስባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምዕራብ ጎንደር የኢትዮጵያ ዋና የቅባት እህሎች ቀበቶ በመሆን የሚታወቀው እንደ ቋራ፣መተማ ዮሃንስ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

በተያያዘም በዚህ አመት ተጨማሪ ምርት እንደሚጠበቅ የዞኑ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በ2021 የመኸር ወቅት ከ130,945 ሄክታር መሬት 930,000 ኩንታል የቅባት እህል መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መረጃ የሚጠቁም ሲሆን በዚህ አመት አሃዙ በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

• @ThinkAbyssinia •