Get Mystery Box with random crypto!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል በዓልን  ምክንያት በማድረግ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው የምሳ | Think Abyssinia

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል በዓልን  ምክንያት በማድረግ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው የምሳ ግብዣ አደረጉ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአሉን ምክንያት በማድረግ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው የሰራዊቱ አባላት በመጎብኘት  የተለያዩ ድጋፎችንና  የምሳ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ‹‹በእናንተ መሃል ተገኝቶ በዓልን ማሳለፍ  ከክብርም በላይ ክብር ነው፤ እናንተ የአገራችን ጀግኖች የአገራችን አርማ  ናችሁ"ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በገጠማት ፈተናዎች ሁሉ ፀንታ መሻገር እንድትችል ከስጦታ ሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ በመስጠት ሃገራችሁን ያፀናችሁ በመሆናችሁ ከእናንተ ጋር መሆን በእጅጉ ያስደስተናል  ሲሉም ጨምረዋል፡፡

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •