Get Mystery Box with random crypto!

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች 1፤በትግራይ በድሮን ጥቃት ፍንጣሪ ተሽከርካሪው መመታቱን የዓለ | Think Abyssinia

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤በትግራይ በድሮን ጥቃት ፍንጣሪ ተሽከርካሪው መመታቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የድሮን ጥቃቱን ተከትሎ በተፈጠረ ፍንጣሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሠራተኛ በሆነው አሽከርካሪ ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በተሽከርካሪው ላይም ቀላል ጉዳት ማጋጠሙን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ተሽከርካሪው ጦርነቱን ተከትሎ በትግራይ ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች ምግብ እያደረሰ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።

2፤አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከተመድ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ።

ምክክሩም በክልሉ እየተከናወነ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችና በክልሉ የሚኖሩ የአቅመ ደካማ ማህበረሰብ ክፍል ኑሮ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። የሁለቱ ወገኖች የስራ ኃላፊዎች በአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ምላሽ በሚሰጥበትና በክልሉ የሚገኙና ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ህይወትን በዘላቂነት የሚቀይርበት ሁኔታዎች ላይ ከመግባባት መደረሱም ነው የተገለጸው።

3፤ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ  "ሊድ" የተሰኘ የሶስት አመት አዲስ  የዕድገት ስትራቴጂ ይፋ አደረገ።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ አዲሱ ስትራቴጂ ከ2011 ጀምሮ እስከ ሰኔ 2014 ድረስ ሲያገለግል የነበረውን ብሪጅ የተሠኘው ስትራቴጂ  የተካ ነው ብለዋል። አዲሱ ሊድ የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም የሶስት አመት ዕቅድ ስትራቴጂ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

4፤በኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ እየተስፋፋ መሆኑ ተነገረ።

ከአንድ ሳምንት በፊት በበሽታው የተያዘ ግለሰብ በተገኘባት ኡጋንዳ በኢቦላ እንደተያዙ የሚጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳለው አስካሁን 34 በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ ሲገልጽ፣ 21 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መሞታቸውን ገልጿል። ኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ ሲያጋጥማት ይህ ለአራተኛው ጊዜ ነው።

5፤የኬንያው ፕሬዝደንት የድርቅ ተጽእኖን ለመቋቋም ግብረኃይል እንዲቋቋም አዘዙ።

በቅርብ የተመረጡት የኬንያወ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ድርቅ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችል ግብረኃይል እንዲያቋቁም ለምክትላቸው ትእዛት ሰጥተዋል፡ ዊሊያም ሩቶ ይህን ያሉት ምርጫ ማሸነፋቸውን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የምስጋና መርሃግብር ላይ ነው፡፡ በኬንያ ከ36 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በድርቅ ተጠቅተዋል

6፤ኢትዮጵያና ሱዳን በወዳጅነት ጨዋታ አቻ ተለያዩ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአቋም መለኪያ ጨዋታ ከሱዳን ጋር ዛሬ ከቀኑ 10:00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጫውቶ ሁለት አቻ ተለያይቷል። ለዋልያዎቹ ሁለቱን ጎሎች ዳዋ ሆቴሳና ቸርነት ጉግሳ አስቆጥረዋል።

መልካም የደመራ በዓል
• @ThinkAbyssinia •