Get Mystery Box with random crypto!

የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ተቸግረዋል (በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ) መስፍን ጌታቸው ' ሰው ለ | Think Abyssinia

የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ተቸግረዋል

(በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)

መስፍን ጌታቸው " ሰው ለሰው "ን ሲጀምር "ሎሚ ፒክቸርስ" የሚባል ድርጅት ነበረው። በሚወዳቸው እናቱ ስም ያቋቋመው ነው። ሎሚናት የእናቱ ስም ነው ።

አሁን ወ/ሮ ሎሚናት ገ/መስቀል ተቸግረዋል። አንድ የሚደግፋቸው ልጃቸው ትልቁ ደራሲ መስፍን ጌታቸው ሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም. ሞተባቸው ። መስፍኔ አንድ የማይደራደርበት መሀላ ነበረው ፤ " ሎሚናት ትሙት ! " የሚል ። እሳቸው ናቸው የተቸገሩት ። የተቸገሩት የሚኖሩበት ቤት ነው ። በወር 3,500 ብር የሚከፈልባት አንዲት ክፍል ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት ። ምንም ቋሚ ገቢ ለሌላቸው እናት በወር 3,500 ብር ማግኘት ጭንቅ ሆኖባቸዋል ።
"ልጄ ቤት ኪራዩ ከመቸው እንደሚደርስ አላውቅም " ነው ያሉኝ ።

ወ/ሮ ሎሚናት ከልጃቸው መስፍን ጌታቸው ሞት በኋላ በወዳጅ ጓደኞቹ ተረስተው ፣ ማንም " እንዴት ነው የሚኖሩት ? " የሚላቸው አጥተው የበጎ አድራጊዎችን እጅ እያዩ ለመኖር ተገደዋል ።

ልጃቸው መስፍን ጌታቸው ስለቋሚ ንብረት ሳያስብ ፣ በሰው እንደተከበበ ፣ ወዳጀ ብዙ ሆኖ ነው የኖረው ። እናቱ ግን አሁን ማንም ጠያቂ አጥተው በአንዲት 3 × 3 በሆነች ቤት ውስጥ ይኖራሉ ። እሷን ቤትም ከግለሰብ የተከራዩዋት ናት ። ከልጃቸው ጓደኞች ተዋናይት ረቂቅ ተሾመ እስካሁን በሁለት ዙር መቶ ሀያ ስምንት ሺህ ብር ልካ ሕይወታቸውን ከከፋ ውድቀት ታድጋለች ። ጣሊያን ሀገር የሚኖረው አብሮ አደግ ጓደኛው ባዩ ተሾመ የቻለውን እያደረገ የጓደኝነት ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል ። ሌሎች ጥቂት ወዳጆቹም መጠነኛ እገዛ አድርገዋል ።

እናት ሎሚናት መስፍኔ ካረፈ ዓመት ከአምስት ወር የኖሩት በዚህ ነው ። ወ/ሮ ሎሚናት የረቂቅ እና ባዩን ስም አንስተው አይጠግቡም ። ማንም ደጋፊና የእኔ የሚሉት ቤት የሌላቸው እናት በወር ይህቺኑ ኪራይ መክፈል አቅቷቸው በሰቀቀን ሕይወታቸውን እየገፉ ይገኛሉ ። እኚህ እናት ችግራቸውን ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲያቀርቡላቸው ለመስፍኔ የቅርብ ወዳጆች እየደወሉ ቢማፀኑም ማንም ይህን ሊያደርግላቸው አልቻለም ።

ሚዲያ ላይ ቀርበው ችግራቸውን ለመግለጽ ቢፈልጉና ቢሞክሩም ሆን ተብሎ በሚሰራ ተንኮል ይህም እንዳይሳካ ተደርጓል። በርካታ ችግረኛ ዜጎች በሚዲያው እየቀረቡ ሲታገዙ ብናይም የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ግን ለጥቂት ሰዎች ክብር ሲባል በኔትዎርክ የትም ሚዲያ ላይ እንዳይቀርቡና ከችግራቸው ጋር እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል።

እኔ ራሴ ለሁለት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ( አዘጋጆች ) አሳውቄ በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ እንዲዳፈን ተደርጓል ። ያሳዝናል ። እጅግ ልብ ይሰብራልም ። ጉዳዩ ብዙ ዝርዝር አሳዛኝ ገጽታ አለው ። ለጊዜው እንለፈው ። ለዚህ ነው  ወደዘጋሁት የፌስቡክ ገጽ ያለጊዜዬ እንድመለስ የተገደድኩት ። ለምን ይህ በደል ይሰራል ? ትናንት መስፍን ጌታቸው በሕይወት ነበረ ፤ ዛሬ የለም ። ነገ ደግሞ የቀን ጉዳይ ካልሆነ ሁላችንም የለንም ።

ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ፦
****

እኔ አይደለሁም ይህን የምለው ። " ልጄ ልጄ እንደምንም ችግሬን ለአዳነች አቤቤ የሚያደርስልኝ ቢገኝ ደሳሳ ማዕድ ቤት እንኳ ብትሰጠኝ አጽድቼ እገባበታለሁ ። ቤት ኪራዩን አልቻልኩትም ። ከመቼው አለፈ ሳልለው ወሩ ይደርሳል ። ምን ላድርግ ? ጨነቀኝ ። ሰዎች የሚሰጡኝን ለሆዴ ላድርገው ለቤት ኪራይ ? እንደው ለአዳነች ብትነግሩልኝ አትጨክንብኝም ።

ቢሮዋ የሚወስደኝ ባገኝ እግሯ ስር ወድቄ በተማጸንኳት " ያሉኝ አጋዥ ያጡት የአንድ ትልቅ ደራሲ እናት ናቸው ። መስፍን ጌታቸው ( ነፍሱን ይማርና ) ከእርስዎ ጋር የብዙ ሚሊዮን ብር ስራ ተነጋግሮ ( ምናልባትም ተፈራርሞ ) ሞት ቀደመው ። አሁን የእሱ እናት ናቸው መጠጊያ ቤት አጥተው ችግር ላይ የወደቁት ።

ክብርት ከንቲባ ደራሲ መስፍን ጌታቸው የሀገርና የጥበብ ባለውለታ ፣ የብዙዎቻችን ወዳጅ ፣ ባለውለታና ለበርካታ ተዋንያን መታወቅና ዝና መጨመር ባለድርሻ ቢሆንም እኛ ሁላችን ወዳጅነቱን ክደናል ። ውለታውን በልተናል ። ( ለመዋጥ ቢመርም እውነታው ይህ ነው ) ለዚህ ነው ጉዳዩ እርስዎ ዘንድ የደረሰው ። የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ድምጽ ለዓመት ከአምስት ወር ቢታፈንም አሁን ግን ይበቃል ። እባክዎ ክብርት ከንቲባ ሌላ ሳይሆን አንዲት ክፍል የቀበሌ ቤት እንኳ ይስጧቸውና ለእኚህ እናት እፎይታን ይስጡልን ። ሌላ ምንም ባያደርጉም በፀሎታቸው ሁሉ አይረሱዎትም ። እባክዎ ክብርትነትዎ ።

ለወዳጆቹና የስራዎቹ አድናቂዎቹ ፦

የደራሲው እናት " ዋና ጉዳዬ አንዲት አንገት ማስገቢያ ደሳሳ ጎጆ ናት " ይበሉ እንጂ እውነታው መከታቸው የነበረው ልጃቸውን በሞት ተነጥቀው ማንም ደጋፊ የላቸውም ። እስከዛሬ አውቀን ምንም ያላደረግን ወዳጆቹም እንሁን ምሥጢሩ ባለመውጣቱ ያላወቃችሁ ከስር ባለው የባንክ ቁጥር የቻልነውን እናድርግላቸው ። በስም ባይለዩዋችሉም ለሰጪዎቻቸው ሁሉ ይፀልዩላችኋል ። እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉን ያያል ።

ሎሚናት ገ/መስቀል ቢራቱ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000034499865

ስለ ፈጣሪ ብላችሁ ፦

1 - ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምትቀርቡ ሁሉ ይህን የተማጽኖ አቤቱታ አድርሱላቸው ።

2 - ብዙሀን መገናኛዎች ከግለሰቦች ሳይሆኑ ከእውነትና ከፍትሕ ጎን ቁሙ ።

3 - ይህን መልዕክት ያያችሁ ሁሉ ሼር ሳታደርጉ አትለፉ ። በእግዚአብሔር ስም።

#SHARE
• @ThinkAbyssinia •