Get Mystery Box with random crypto!

በዎላይታ ብሔር ዘንድ የሚከበረው የጊፋታ ክብረ በዓል 'ጊፋታ' የእርቅ መሰረትና የሰላም ተምሳ | Think Abyssinia

በዎላይታ ብሔር ዘንድ የሚከበረው የጊፋታ ክብረ በዓል

"ጊፋታ" የእርቅ መሰረትና የሰላም ተምሳሌት ሲሆን በዓሉን በቁርሾና ጥላቻ ማክበር የማይቻል በመሆኑ በጊፋታ ፍቅር ይቀነቀናል፤ የጊፋታን በዓል በዓለም በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

በዎላይታ ብሔር ዘንድ የሚከበረው የጊፋታ ክብረ በዓል ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ በዓል ነው። መስከረም ወር በገባ ከ14-20 መካከል በሚውለው እሁድ ዕለት አዲሱን ዓመት በድምቀት ይቀበሉታል። ይህ እሁድ እለት የአዲስ ዓመት ቀን ሲሆን ስሙም "ሹሃ ወጋ" ይሰኛል ትርጉሙም የእርድ እሁድ እንደማለት ነው፡፡

ጊፋታ ማለት ባይራ (ታላቅ)፣ “መጀመሪያ” እንደ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ጊፋታ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡  ከቆጮ የሚሰራው “ባጭራ” የተባለው የሆድ መፍታቻ ምግብ ደግሞ ለበዓሉ ዋዜማ ይዘጋጃል፡፡

• @ThinkAbyssinia •