Get Mystery Box with random crypto!

#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች 1፤መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ። የኢት | Think Abyssinia

#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና ታሳቢ በማድረግ፣ በቅጥር ገቢ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ እንዲቀንስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ አአቅርቧል፡፡ ለኑሮ ውድነቱ መንግሥትን ‹‹በጀት አውጥተህ ደጉም›› ማለት ስለማይቻል በሌሎችም አገሮች የኑሮ ውድነት ሲከሰት እንደሚደረገው ሁሉ የሥራ ግብር ምጣኔ እንዲቀነስ ኮርፖሬሽኑ ጠይቋል።

2፤ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት ለአፍሪካ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ጠየቀች።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት 77ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት በቂ ቦታ ሊሰጣትና ትክክለኛው የአፍሪካ ድምጽ ሊሰማ ይገባል ብለዋል። በመድረኩ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያካሄደች ላለችው ጥረት እውቅና እና ድጋፍ ሊሰጠው እንደሚገባም አንስተዋል።

3፥የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ እየዋለ ነው ተባለ።

ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው ተልዕኮ ውጪ ለሆነ የፖለቲካ ሥራ እንደሚውል፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በተመረጡ 61 ተቋማት ላይ ያደረገው የጥናት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ከመምህራን ልማትና ከአሠልጣኞች ምልመላ ጋር በተገናኘ፣ የዘመድና የፓርቲ አሠራር፣ እንዲሁም አድልኦና ጉቦ የመቀበል አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል ብሏል፡፡

4፤በሶማሊላንድ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተራዘመ።

በተገንጣይ ሶማሊላንድ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ “በቴክኒካል እና በፋይናንሺያል ምክንያቶች” መራዘሙን ምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ምርጫውን ለካሄድ የሚችልበትን ቀን ባይቆርጡም የሚካሄድበትን ጊዜ ግን በዘጠኝ ወራት አራዝሟል።

5፤የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን ያገኛል።

አስራ ስድስተኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚደረጉ መርሐ ግብሮች ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል። ለሶስተኛ ደረጃ በሚደረግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ከቀኑ 7:00 ላይ ሲጫወቱ ፈረሰኞቹ ለዋንጫው ከመቻል ጋር ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይፋለማሉ።

• @ThinkAbyssinia •