Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለሜትር ታክሲ ተሸከርካሪዎች የቀረጥ ነጻ ድጋፍ ማቆሙን አስታ | Think Abyssinia

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለሜትር ታክሲ ተሸከርካሪዎች የቀረጥ ነጻ ድጋፍ ማቆሙን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ አስማረ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እስኪ ተጠየቁ ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት፣ ቢሮው ከዚህ ቀደም በሜትር ታክሲ አገልግሎት ዘርፍ ለመሰማራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ለነበሩ ማህበራትና ግለሰቦች ተሸከርካሪዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ለገንዘብ ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ሲጽፍ ቆይቷል።

ሆኖም፣ ቢሮው በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የሜትር ታክሲ ተሸከርካሪዎች ቁጥር በቂ ሆኖ በማግኘቱ የቀረጥ ነፃ ድጋፍ መስጠት ስለማቆሙ ኃላፊው ተናግረዋል። በሜትር ታክሲ ዘርፍ መሰማራት የሚፈልግ ማንኛውም አካል የቀረጥ ነጻ መብት ሳይጠይቅ ተሸከርካሪዎችን ማስገባት ይችላል ያሉት ኃላፊው፣ በብዙሃን ትራንስፖርት ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ግለሰቦችና ማህበራት ግን የቀረጥ ነጻ መብት እንዲያገኙ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት።

via - ebc
• @ThinkAbyssinia •