Get Mystery Box with random crypto!

ብሄራዊ ባንክ በጥቁር ገበያው ተዋንያን ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ። ዛሬ የኢትዮጵ | Think Abyssinia

ብሄራዊ ባንክ በጥቁር ገበያው ተዋንያን ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሕገወጥ የሐዋላ ስራ የተሰማሩ ሰዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። በዚህም 391 የሚደርሱ ሕገወጥ የሐዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው መዘጋቱንና የግለሠቦቹ ስም ዝርዝር ለፍትሕ ሚኒስቴር ተልኮ ክስ የመመስረት ሂደቱ እንደሚጀመር አስረድተዋል።

በህገ ወጥ መልኩ በጥቁር_ገበያ ላይ በተሠማሩ አካላት ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል። አክለውም በባንክ ቤቶች ውስጥ ያሉ የባንክ ኃላፊዎችና ሰራተኞችም በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አሉ በነዚህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ነው በመግለጫቸው ያነሱት። ይህን ሕገወጥ ድርጊት ለሚጠቁሙ ዜጎች የወሮታ አከፋፈል ስርዓት መዘጋጀቱም ተነግሯል።

via - EPA
• @ThinkAbyssinia •