Get Mystery Box with random crypto!

በድሬዳዋ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ውሳኔ ለ5 ወራት ተራዘመ። | Think Abyssinia

በድሬዳዋ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ውሳኔ ለ5 ወራት ተራዘመ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በሳምንታዊ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ አስተዳደሩ ከሰኔ 2014ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ወራት የቤት ኪራይ መጨመርና ተከራይን ማስወጣት የሚከለክል ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ እና የኑሮ ውድነት ከግምት በማስገባት በተከራይ ላይ የኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ከቤት ማስወጣት የሚከለክለው ውሳኔ ለሚቀጥሉት አምስት ወራት ተፈጻሚ ሆኖ እንዲቀጥል ካቢኔው ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በተጨማሪም ካቢኔው በገበያ ትስስር ለኢንተርፕራይዞች ስለሚሰጥ የዋስትና ሽፋን መመሪያ እና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ፍኖተ ካርታን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የድሬዳዋ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

via - fbc
• @ThinkAbyssinia •