Get Mystery Box with random crypto!

ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አሜሪካ በምትልከው የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገች። በሳውዲ መንግስት ቁጥጥ | Think Abyssinia

ሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አሜሪካ በምትልከው የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገች።

በሳውዲ መንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ሳዑዲ አራምኮ በህዳር ወር ወደ አሜሪካ በሚልከው ድፍድፍ ነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ የ20 ሳንቲም ጭማሪ ሲያደርግ ባንፃሩ ዋነኛ የገበያ መዳረሻው በሆነው እስያ ገበያ ላይ ምንም ጭማሪ አለማድረጉን ብሉምበርግ አስነብቧል። አሜሪካ ውሳኔውን አርቆ አለማየት ነው ስትል ተችታለች፡፡

ሩሲያ ላይ በተጣለባት ማዕቀብ የተነሳ ከሰኔ ወር ጀምሮ የዓለም አቀፉ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ መቀነሱ ተገልጿል፡፡ ይሁንና በበርሜል 90 ዶላር የሚጠጋው አሁን ያለው ዋጋ ግን በዚህ አመት ወደ 20 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል፡፡ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚታየው የዋጋ ግሽበት አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሆነ የአር ቲ ዘገባ ያመላክታል።

• @ThinkAbyssinia •