Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ስንዴ እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት ተደረሰ። ስምምነቱ የተደረሰው የኬንያ | Think Abyssinia

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ስንዴ እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት ተደረሰ።

ስምምነቱ የተደረሰው የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ የኬንያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ የስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በኬንያ የተከሰተውን የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ከስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በተጨማሪ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አቅም ለመጠቀም በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡በአጠቃላይ የሁለቱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የድንበር ተሻጋሪ ንግድን ለማሳደግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

via - fbc
• @ThinkAbyssinia •