Get Mystery Box with random crypto!

የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የደራሼ | Think Abyssinia

የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጆበርና አሰፋ በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።ሀላፊው የተገደሉት ያለፈው ቅዳሜ ማለዳ ላይ ሲሆን፤የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንደተናገሩት ከአካባቢው ባለስልጣን ግድያ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአካባቢው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣት ላይ ግድያ ሲፈፀም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው በመጋቢት ወር በሰገን ወረዳ በኮንሶ ዞን ዙሪያ ወረዳ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ገረሙ ገለቦ በአንድ ሆቴል ውስጥ ከጓደኞቻቸው ጋር ሲመገቡ በጥይት መገደላቸው ታውቋል።

[DW]

• @ThinkAbyssinia •