Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ህንድ በቡድን ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል ብላ ለመክሰስ ፖሊስ ጣቢያ የሄደችው የ13 ዓመት ታ | Think Abyssinia

በሰሜን ህንድ በቡድን ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል ብላ ለመክሰስ ፖሊስ ጣቢያ የሄደችው የ13 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መደፈሯ ቁጣን ቀስቅሷል።

አሁን ላይ ታዳጊዋን የደፈረው ፖሊስ ከስራው የተገደ ሲሆን ፤ በቁጥጥር ስርም ውሏል።

ታዳጊዋ ባለፈው ወር በ4 ወንዶች መደፈሯን ተናግራለች፡፡ የታዳጊዋ የመደፈር ዜና በመላ ህንድ ትልቅ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።

የታዳጊዋ ወላጅ ባቀረቡት ክስ፤ አራቱ ወንዶች ሴት ልጃቸውን የደፈሯት ለአራት ቀናት ያክል ማደያ ወደ ተባለ ግዛት ወስደው እቤት ውስጥ በመዝጋት ነበር ብሏል፡፡

አራቱም ወንዶች ለአራት ቀናት ከደፈሯት በኋላ ወደ መኖሪያ አከባቢዋ መልሰው ጥለዋት መሰወራቸውንም ነው ወላጅ አባቷ የገለጹት፡፡

በሚቀጠለው ቀን ታዳጊዋ ከአክስቷ ጋር በመሆን ክስ ለመመስረት ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደች ቢሆንም፤ በፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ እንደተደፈረች ኤን-ዲቲ-ቪ የተባለ የህንድ ቻናል ዘግቧል፡፡

ዜናውን ተከትሎ በግዛቱ ያሉትን ህጎች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው በመነገር ላይ ያለው፡፡

የህንድ ኮንግረስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፕሪያንካ ጋንዲ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ‘‘ ፖሊስ ጣቢያዎች ለሴቶች ደህንነት አስተማማኝ ካልሆኑ ፤ ሴቶች ታዲያ የት ሄደው ይከሳሉ? ’’ የሚል ትችት አዘል መልእክት አጋርቷል፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ /ND TV

• @ThinkAbyssinia •