ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በእጅጉ መባባሳቸውን ለፓርላማው ባቀረበው የ9 ወራት ሪፖርት ገለፀ ጸጥታ ኃይሎች የሚፈጽሙት ከፍርድ ውጭ ግድያ፣ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀም፣ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር፣ የተራዘመ የቅድመ-ክስ እስር፣ ባንዳንድ የእስር ቦታዎች ያለ ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ የሕጻናት ሕገወጥ እስር እና ጋዜጠኞችን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችንና የማኅበረሰብ አንቂዎችን አስገድዶ መሰወር ተደጋግሞ መከሰቱን ኮሚሽኑ ገልጧል። ከሰሜኑ ጦርነት፣ ከብሄር ማንነት፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር፣ ከአስተዳደር ወሰንና ከሐይማኖት ጋር የተያያዙ ግጭቶች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስከተላቸውን ኮሚሽኑ ጨምሮ ጠቅሷል። wazema radio • @ThinkAbyssinia • 10.6K views15:46