Get Mystery Box with random crypto!

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የ 7.2 ሚሊዮን ቤቶች አቅድ በዝርዝር ሲታይ የከተማ እና | Think Abyssinia

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የ 7.2 ሚሊዮን ቤቶች አቅድ በዝርዝር ሲታይ

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በሪል ስቴት የልማት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ትላንት ማክሰኞ ሚያዝያ 25፤ 2014 ባደረጉት ንግግር፤ መንግስት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 7.2 ሚሊዮን ቤቶች በከተማ እና በገጠር ለመገንባት አቅዶ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል። በከተሞች ለመገንባት ከተያዘው 4.4 ሚሊዮን ቤት የግል ሴክተሩ 80 በመቶውን ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም በእቅድ የያዛቸውን የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መጨረስ አለመቻሉን የታዘቡ ባለሙያዎች፤ በሚኒስትሯ የተገለጸው እቅድ ተግባራዊነት ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ሲገልጹ ተስተውለዋል። ባለሙያዎቹ እቅዱ “ከምናብ የዘለለ” አለመሆኑን በቁጥር ጭምር አስደግፈው ቢሞግቱም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ዓመት ይፋ ያደረገው የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ ግን ከሚኒስትሯ ገለጻ ጋር የተስማማ አሃዝን አስቀምጧል።

በልማት እቅዱ መሰረት፤ ከ2013 እስከ 2022 ባሉት አስር ዓመታት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ 7,800,000 ገደማ የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ። ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ ውስጥ 4.4 ሚሊዮኑ በከተማ፣ ወደ ሶስት ሚሊዮን ገደማ የሚጠጉት ደግሞ በገጠር ማዕከላት እንዲገነቡ መታቀዱን ሰነዱ ያመለክታል።


(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
• @ThinkAbyssinia •