Get Mystery Box with random crypto!

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች 1፤በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታው ከተጠበቀው በታች መሆኑ ተገለፀ | Think Abyssinia

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታው ከተጠበቀው በታች መሆኑ ተገለፀ።

በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር አትንኩት መዝገቡ ተፋላሚ ሀይሎች የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፉ ወዲህ ወደ ትግራይ የገባው የሰብዓዊ እርዳታ መጠን ከሚጠበቀው ከ5 በመቶ በታች ነው ብለዋል።
ሀላፊው እንደሚሉት ወደ ትግራይ በየቀኑ አንድ መቶ እርዳታ የጫኑ መኪኖች እንደሚገቡ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ ተኩስ አቁሙ ከተደረገ ከአንድ ወር በላይ በሆነ ጊዜ በአጠቃላይ የገቡ እርዳታ የጫኑ መኪኖች ቁጥር 173 ብቻ ናቸው ያሉ ሲሆን በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከ6 ነጥብ 3 ሚልየን በላይ ዜጎች እርዳታ ፈላጊ ናቸው ሲሉም አክለዋል።
ተስፋ የተጣለበት የሕይወት አድን ሰብዓዊ እርዳታ ስራ በሚፈለገው እናበተጠበቀው ሁኔታ እየሄደ አይደለም ብለዋል።

2፤ኢትዮጵያዊያን ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎችን በጋራ
እንዲቃወሙ አብን ጥሪ አቀረበ፡፡

ፓርቲው ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ ቢጸድቁ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ እና ረቂቅ ሕጎቹን ለማዘጋጀት ያስፈለገበትን ዓላማ በጥንቃቄ እና በተከታታይ መመርመሩን በመግለፅ መግለጫ አውጥቷል፡፡
መግለጫው ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ የከፋ ደም መፋሰስን፣ መቆሚያ የሌለው ግጭትን እና የከፋ አምባገነናዊ ሥርዓትን ከመፍጠር ውጭ የተሻለ መፍትሄ እንደማያመጡ ጠቅሶ በሀገሪቱ በተፈጠረው ችግር ተጎጂዎችን እና ጥፋተኞችን በአንድ የሚያይ በመኾኑ ጉዳቱ ሀገራዊ ነውና ተገቢነቱ ላይ እንደማያምን አብን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ እንዳይጸድቁ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ አሳስቧል።

3፤ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የወጪ ቅነሳን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ገንዘብ ሚኒሰቴር አሳሰበ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የወጪ ቅነሳ ጉዳይ የ2015 በጀት አመት አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በበጀት አመቱ አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩና ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸው ንብረት ታውቆ በአንድ የመረጃ ቋጥ ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ የክትትልና የቁጥጥር ስርአት እንደሚዘረጋ ገልጸዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒሰቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው የፋይናንስ ስርአቱን በህጉ መሰረት ተግባራዊ ባላደረጉ የተቋማት ኃላፊዎችና ባለሞያዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡

4፤ከሳዑዲ አረብያ 1ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ወደሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች ውስጥ አምስት ህጻናትና 1ሺህ24 ወንዶች መሆናቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል ተብሏል።

5፤ የዩክሬን አርሶ አደሮች የጥይት መከላከያ ለብሰው ወደ እርሻቸው መመለሳቸው ተነገረ።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የስንዴ ልማት ስራዎች የሚከናወኑበት ወቅት ላይ በመሆኑ ስንዴ አምራቾችን እየፈተነ ሲሆን በደቡባዊ ክልል የሚኖሩ የዩክሬን አርሶ አደሮች ማሳቸውን ለማረስ የጥይት መከላከያ እየለበሱ መሆኑ ታውቋል።
ይህ የስንዴ አዝመራ ወቅት እንዳያልፋቸው የሰጉ ዩክሬናዊያን ገበሬዎች የጥይት መከላከያ ጃኬት እና ሄልሜት አድርገው ስንዴ ማልማታቸውን ቀጥለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

6፤ሪያል ማድሪድን መግጠምና መበቀል እፈልጋለው ሲል መሀመድ ሳላ ተናገረ።

የመርሲሳይዱ ክለብ ግብፃዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሞሀመድ ሳላህ ሪያል ማድሪድን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ መግጠም እንደሚፈልግ ገልጿል ።
ሞሀመድ ሳላህ ሲናገር " በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሪያል ማድሪድን መግጠም እፈልጋለው ፤ በ 2018 በፍፃሜው በሪያል ማድሪድ ተሸንፈናል አሁን ከእነሱ ጋር ከተገናኘን የምናሸንፋቸውና የምንበቀላቸው ይመስለኛል" ሲል ተደምጧል ።
በ2018 ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳቱ ይታወሳል። ዛሬ ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን አሸንፎ ለፍፃሜ ከደረሰ ሊቨርፑል የሚገጥም ይሆናል።



• @ThinkAbyssinia •