Get Mystery Box with random crypto!

ተስፈኛው ታዳጊ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገለት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ባርሴሎ | Think Abyssinia

ተስፈኛው ታዳጊ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገለት


የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ባርሴሎና ከተማ በሚገኘዉ ቢ1 አካዳሚ የመሰልጠን እድልን ላገኘው ታዳጊ ይበልጣል ኤልያስ የአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

የሊጉ የቦርድ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ "የሀገራችን ተጫዋቾች በውጭ ወጥተው እንዲጫወቱ ማድረግ አንደኛው ራዕያችን ነው። ለአንተም የምንመኝልህ ይህንን ዕድል ወደ ፍሬያማ ነገር እንድትለውጠው እና በአውሮፓ ክለቦች ላይ እንድንመለከተህ ነው።" ያሉ ሲሆን: ሌሎች ታዳጊዎች ይህንን መሰል ነገር ይዘው ከቀረቡ አክስዮን ማህበሩ የቻለውን ያክል ለማገዝ ሁሌም በሩ ክፍት ነው ሲሉም አክለዋል።

ከአክሲዮን ማህበሩ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ታዳጊው ይበልጣል ኤሊያስ በበኩሉ "እኔን ያገዙኝን ሰዎች የማስደስተው በትልቅ ደረጃ ራሴን በማብቃት መሆኑን ስለማምን: ጠንክሬ በመስራት በቅርቡ በሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና ዋናው ቡድን ትመለከቱኛላችሁ" ብሏል።


• @ThinkAbyssinia •