Get Mystery Box with random crypto!

በዩክሬን ዶኔስክ ግዛት የሚገኘው የነዳጅ ማከማቻ ጥቃት ደረሰበት በዶኔስክ ሪፐብሊክ ውስጥ በ | Think Abyssinia

በዩክሬን ዶኔስክ ግዛት የሚገኘው የነዳጅ ማከማቻ ጥቃት ደረሰበት


በዶኔስክ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኘው ማኬዬቭካ ከተማ ላይ የዩክሬን ጦር ጥቃት በመፈጸሙ አራት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንኮች መቃጠላቸውን አር ቲ ኒዉስ የአካባቢው ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

እያንዳንዱ ታንክ እስከ 5 ሽህ ኪዩቢክ ሜትር ነዳጅ ሊይዝ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፣ የዩክሬን መገናኛ ብዙሀን የነዳጅ ማከማቻዉ ጥቃት የተፈጸመበት ለሩሲያ ሃይሎች ነዳጅ እየሸጠ ስለነበር ነዉ ብሏል።

የዩክሬን መከላከያ ሰራዊት በፈጸመው ጥቃት አንድ ሰው መሞቱን እና ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውም ተገልጿል፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል በቀጠለው ጦርነት በከተማዋ ከፍተኛ የንብረት ዉድመት መከሰቱንና በርካታ ሰዎች ከተማዋን ለቀዉ ለስደት መዳረጋቸዉን መረጃዉ አመልክቷል፡፡

RT_News


• @ThinkAbyssinia •