Get Mystery Box with random crypto!

160 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘችው ባለሙያ ክስ ተመሰረተባት ዐቃቤ ህግ በንፋ | Think Abyssinia

160 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘችው ባለሙያ ክስ ተመሰረተባት

ዐቃቤ ህግ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት መኔጅመንት ባለሙያ ሆና ስትሰራ 160 ሺ ብር ጉቦ በመቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል በፈፀመች ግለሰብ ላይ ክስ መስርቷል::

ወ/ሮ ሃብታምነሽ ሊሞና የተባለችው ተከሳሽ የሙስና ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10 (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፏ ነው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባት።

ተከሳሿ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 በተበዳይ ስም ተመዝግቦ ይገኝ የነበረ ይዞታ በሽያጭ ወደ 4ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በመተላለፉ የሥም ዝውውር እንዲደረግ ለጽ/ቤቱ በቀረበው የአገልግሎት ጥያቄ መሰረት አስፈላጊ መስፈርቶች ሁሉ ተሟልተው እያለ ሚያዝያ 03 ቀን 2014 ዓ.ም የሥም ዝውውር ከተፈጸመ በኋላ ገዢዎችን በመወከል ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን “ካርታው ተሰርቷል ገንዘብ ካላመጣህ ግን ወጪ አድርገን አንሰጥህም” በማለት 160,000 ብር ጉቦ በመጠየቅና ስትቀበልም እጅ ከፍንጅ የተያዘች በመሆኑ በፈፀመችው ጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባታል ፡፡

ተከሳሿ ትላንት ግንቦት 03/2014 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት ቀርባ የክስ ቻርጅ አንዲደርሳት ከተደረገ በኋላ ክሱ በንባብ ተሰምቷል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የምታቀርበው የክስ መቃወሚያ ካለ ለመጠባበቅ ለግንቦት 05/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰቷል ።።

ፍትሕ ሚ/ር

• @ThinkAbyssinia •