Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-09 20:03:09
9 ኛው የጉማ አዋርድ ዝግጅት በእስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በኪነጥበብ ዘርፍ ላይ ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ጥበበኞች በመሸለም የሚታወቀው ጉማ አዋርድ ሰኔ 02/10/2015 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል የሰማያዊ ምንጣፍ ጉማ የፊልም ሽልማት እየተካሄደ ነው።

በዘንድሮ ጉማ አዋርድ ሽልማት የአርያ ሰብ ከያኒ በሚል ዘርፍ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ እየሠራች የምትገኘው እና በትወናው ዘርፍ በርከት ያሉ ስራዎችን ያበረከተችው አርቲስት መሠረት መብራቴ ልዩ ተሸላሚ እንደምትሆን እንዲሁም የህይወት ዘመን ተሸላሚ አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው አርቲስት ኪሮስ ሃይለስላሴ የሄርሜላ ተሸላሚ የአቢሲኒያ የስነ ጥበብ መስራች የሆኑት ወ/ሮ ገነት ከበደ ተሸላሚዎች መሆናቸው መገለፁ የሚታወስ ነው ።

በዘንድሮ የጉማ አዋርድ በ24 ዘርፎች በየዘርፋ 5 እጩዎችን አቅርቧል። የአንዳንድ አርቲስቶች ፎቶ ደግሞ መልክቱ ሃያል ነው።
4.0K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 18:14:25
ማንችስተር ሲቲ የደጋፊዎቹን ወጪ ሸፍኖ ወደ ኢስታንቡል እያጓጓዘ ነው

ኢትዮጵያዊያን የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎችም ሙሉ ወጪያቸው በሚደግፉት የእንግሊዙ ክለብ ተሸፍኖ የዘንድሮውን የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ በቱርክ ኢስታምቡል ተገኝተው ክለባቸውን ለመመልከት እድሉን አግኝተዋል።
5.1K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 18:00:21
ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች፤ በአንድ ወር ውስጥ ቤቶቹን እንዲያስረክቡ ቀነ ገደብ ተሰጣቸው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ የተከራዩዋቸውን ቤቶች እንዲያስረክቡ ቀነ ገደብ ማስቀመጡን ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል።

የከተማ አስተዳደሩ የሚረከባቸውን እነዚህን የቀበሌ ቤቶች “የደሃ ደሃ” ተብለው ለተለዩ ነዋሪዎች ለማከፋፈል እቅድ መያዙን ዘገባው አክሏል።
5.1K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:19:09
በባህሬን በአሰሪዋ ተደብድባና ተደፍራ ያረገዘችው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ተወሰነላት

በባህሬን አንዲት ወጣት 4 ዓመት ሙሉ ስትሰራበት የነበረበት ቤት ውስጥ በአሰሪዋ በመደፈር፣ በመደብደብ እና የመግደል ዛቻ ሲደርስባት በመቆየቱና የድረሱልኝ ጥሪዋን በማሰማቷ ምክንያት፤ በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በጋራ በመሆን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማመልከት ፍትሕ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አሰሪዋ “አልደፈርኩም” ብሎ የሕክምና ወረቀት በማቅረብ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ ወጣቷን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፤ ጽ/ቤቱና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከ6 ወራት በላይ በመከራከርና የDNA ምርመራ በማስደረግ በተገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት፤ ወጣቷ የስድስት ወር እርጉዝ መሆኗና የእርሱም ልጅ እንደሆነ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል።

በዚህም መሠረት፤ የወጣቷን እና የልጇንና መብት በማስከበር 64 ሺሕ 800 የባህሬን ዲናር (9 ሚሊዮን 344 ሺሕ 886 ብር) በየአራት ዓመት ክፍያ እንዲከፍል አሰሪው የተስማማ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ አራት ዓመት የሚሆን ቅድመ ክፍያ 14 ሺሕ 200 የባህሬን ዲናር (2 ሚሊዮን 47 ሺሕ 799 ብር) በመቀበል ፍርድ ቤት ፈርሞበት ወጣቷ ፍትህ እንድታገኝ መደረጉን በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አስታውቋል።
5.6K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 15:53:43
ኤሌክትሪሻኑ በልዩ ሎተሪ የ3,5 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነውና በኤሌክትሪሻን ሙያ የተሰማራው አቶ አስቻለው ለገሰ በቆረጡት ልዩ ሎተሪ የ1ኛ ዕጣ የ3,500,000 ብር ዕድለኛ ሆነዋል። አቶ አስቻለው ለገሰ በገንዘቡም ወደ ንግድ ለመሰማራት እንዳሰቡ ተናግረዋል።
5.3K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:56:29
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዪች ከፍተኛ ም/ቤት በዛሬው እለት በመዲናችን አዲስ አበባ በሁሉም መስጂዶች የጁመዐ ሰላት እንደወትሮው ሁሉ በሰላም ተሰግዶ ተጠናቋል!!!

በመላው ከተማችን ባሉ መስጂዶች የጁመዓህ ሰላት በሰላም ተሰግዶ ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አቅጣጫን በመከተል የጁመዐህ ሰላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታችሁን ለጠዋጣችሁ ኢማሞች፣የከተማችን ሙስሊሞች፣የክፍለ ከተማ እና የወረዳ እስልምና ም/ቤቶች እንዲሁም የመስጂድ ኮሚቴዎች ም/ቤታችን ምስጋናውን ያቀርባል።

ከሁሉ በፊት "መስጂዳቻችን አይፈረሱ" በሚል ሰላምን የሚያውክ ምንም ነገር ሳይዙ ለተገደሉት ልጆቻችን አላህ በሸሂድነት የቀሸላቸውና የጀነት እንዲያደርጋቸው እንለምነዋለን፣እንዲሁም በክስተቱ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው ልጆቻችን  ፈጣን የሆነ ማገገምን አላህ እምዲሰጣቸው እየለመንን በድጋሚ ለመላው የከተማችን ሙስሊሞች የም/ቤታችንን አመረርና አቅጠሰጨሰ በመቀበል ተግባራዊ በማድረጋችሁና ሰላምን በማስከበራችሁ ም/ቤታችን ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
5.9K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 12:33:34
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 የአውሮፕላኖቹን ብዛት 271 ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ኢስታንቡል በሚገኘው የአይ ኤ ቲ ኤ ኤ ጂ ኤም ፕሮግራም ላይ ከአቪዬሽን ዴይሊ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በዚህም አሁን ላይ ወደ 140 በሚጠጉ አውሮፕላኖች እየተሠራ እንደሆነ አመልክተው ፥ በፈረንጆቹ 2035 ቁጥሩን ወደ 271 አውሮፕላኖች በማሳደግ አገልግሎት ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡ ይህን ለማሳካትም 130 ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንደሚታዘዙ አመላክተዋል።

ከሰኔ 5 ቀን ጀምሮ አየር መንገዱ ከሚያዛቸው 29 አውሮፕላኖች ማለትም 17 የ737 ማክስ፣ አምስት 777ኤፍ ኤስ፣ አንድ 787-9 እና ሥድስት ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በአፍሪካ 63 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት አየር መንገዱ ፥ በአሁኑ ወቅት ያለውን 20 አውሮፕላን ማረፊያዎች ወደ 27 እንደሚያሳድግም ነው የተጠቆመው፡፡
6.0K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 12:22:04
#የሰሌዳ_እለታዊ_የስራ_ጥቆማ

ኢቢሲ ያዘጋጀው ነጋድራስ የስራ ፈጠራ ውድድር የመጀመሪያው ምዕራፍ ምዝገባ እየተካሄደ ነው። ማንኛውም አዲስ የንግድ ሀሳብ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ፕሮቶታይፖች ካላችሁ በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ ተብሏል::

ለመወዳደር የቢዝነስ ፕሮፖዛል ከ1000 ቃላት ያልበለጠ አጭር መግለጫ /concept note/ በማዘጋጀት የመመዝገቢያ ቅፁን መሙላት ትችላላችሁ::

ምዝገባው በኢቢሲ ድረ-ገፅ www.ebc.et በኦንላይን ብቻ የሚሞላ ሲሆን ተከታዩን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) መጠቀም ትችላላችሁ::

https://ebc.et/NegadRasApplicationForm.aspx

መልካም ዕድል!
5.8K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 09:53:05
ጥቁር ምንጣፍ ወይስ አስፋልት ያስባለው አነጋጋሪው የህንድ አስፋልት

በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ጃልና የተሰኘው ወረዳ ነዋሪዎች ለአመታት የመንገድ ይገንባልን ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ አግኝቷል። ነገር ግ ደስታቸውን የቅጽበት ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ክስተት ገጥሟቸዋል ይላል የአልዐይን ዘገባ።

የጠጠር መንገዳቸው የለበሰው አስፋልት በቀላሉ እንደምንጣፍ ሊነሳ የሚችል በሌላ ቋንቋም ጥቁር ምንጣፍ ሆኖ አግኝተውታል።

በእጃቸው ሲያነሱትም ከስሩ ጨርቅ ነገር ለብሶ ከላዩ ላይ በስሱ አሽዋና ሬንጂ ተደርጎበት የተሰራ መሆኑንም ያረጋግጣሉ። መንገዱን የሰራውን ተቋራጭ ሲጠይቁት አዲስ የጀርመን ቴክኖሎጂ ተጠቅሜያለሁ ሲል ተሳልቋል።
6.3K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 09:04:21
አዲሱ የሜሲ ክለብ ኢንተር ሚያሚ የሜሲ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚታይበት የስታዲየም መግቢያ ትኬት ሽያጩ ደርቶለታል ተባለ።

የአሜሪካው ኢንተር ሚያሚ ከሜክሲኮው ክሩዝ አዙል ጋር በሀምሌ ወር መጨረሻ በሚያደርገው ጨዋታ ዝቅተኛው የመግቢያ ትኬት ዋጋ 29 ዶላር ነበር።

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ሚያሚን እንደሚቀላቀል ካሳወቀ በኋላ ግን የትኬት ዋጋወ በአሜሪካ የእግርኳስ ጨዋታ ታሪክ ታይቶ ማይታወቅ መልኩ እጅግ ንሯል።

ፎርብስ ባወጣው መረጃ መሰረት በሜሲ የመጀመሪያ የኢንተር ሚያሚ ጨዋታ ዝቅተኛው የመግቢያ ትኬት እስከ 459  ዶላር ድረስ እየተሸጠ ነው ብሏል።
6.3K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ