Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዪች ከፍተኛ ም/ቤት በዛሬው እለት በመዲናችን አዲስ አበባ በሁሉም መስጂ | ሰሌዳ | Seleda

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዪች ከፍተኛ ም/ቤት በዛሬው እለት በመዲናችን አዲስ አበባ በሁሉም መስጂዶች የጁመዐ ሰላት እንደወትሮው ሁሉ በሰላም ተሰግዶ ተጠናቋል!!!

በመላው ከተማችን ባሉ መስጂዶች የጁመዓህ ሰላት በሰላም ተሰግዶ ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አቅጣጫን በመከተል የጁመዐህ ሰላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታችሁን ለጠዋጣችሁ ኢማሞች፣የከተማችን ሙስሊሞች፣የክፍለ ከተማ እና የወረዳ እስልምና ም/ቤቶች እንዲሁም የመስጂድ ኮሚቴዎች ም/ቤታችን ምስጋናውን ያቀርባል።

ከሁሉ በፊት "መስጂዳቻችን አይፈረሱ" በሚል ሰላምን የሚያውክ ምንም ነገር ሳይዙ ለተገደሉት ልጆቻችን አላህ በሸሂድነት የቀሸላቸውና የጀነት እንዲያደርጋቸው እንለምነዋለን፣እንዲሁም በክስተቱ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው ልጆቻችን  ፈጣን የሆነ ማገገምን አላህ እምዲሰጣቸው እየለመንን በድጋሚ ለመላው የከተማችን ሙስሊሞች የም/ቤታችንን አመረርና አቅጠሰጨሰ በመቀበል ተግባራዊ በማድረጋችሁና ሰላምን በማስከበራችሁ ም/ቤታችን ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት