Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 የአውሮፕላኖቹን ብዛት 271 ለማድረስ እየሰራ መሆኑን | ሰሌዳ | Seleda

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 የአውሮፕላኖቹን ብዛት 271 ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ኢስታንቡል በሚገኘው የአይ ኤ ቲ ኤ ኤ ጂ ኤም ፕሮግራም ላይ ከአቪዬሽን ዴይሊ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በዚህም አሁን ላይ ወደ 140 በሚጠጉ አውሮፕላኖች እየተሠራ እንደሆነ አመልክተው ፥ በፈረንጆቹ 2035 ቁጥሩን ወደ 271 አውሮፕላኖች በማሳደግ አገልግሎት ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡ ይህን ለማሳካትም 130 ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንደሚታዘዙ አመላክተዋል።

ከሰኔ 5 ቀን ጀምሮ አየር መንገዱ ከሚያዛቸው 29 አውሮፕላኖች ማለትም 17 የ737 ማክስ፣ አምስት 777ኤፍ ኤስ፣ አንድ 787-9 እና ሥድስት ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በአፍሪካ 63 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት አየር መንገዱ ፥ በአሁኑ ወቅት ያለውን 20 አውሮፕላን ማረፊያዎች ወደ 27 እንደሚያሳድግም ነው የተጠቆመው፡፡