Get Mystery Box with random crypto!

በባህሬን በአሰሪዋ ተደብድባና ተደፍራ ያረገዘችው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ተወሰነላ | ሰሌዳ | Seleda

በባህሬን በአሰሪዋ ተደብድባና ተደፍራ ያረገዘችው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ተወሰነላት

በባህሬን አንዲት ወጣት 4 ዓመት ሙሉ ስትሰራበት የነበረበት ቤት ውስጥ በአሰሪዋ በመደፈር፣ በመደብደብ እና የመግደል ዛቻ ሲደርስባት በመቆየቱና የድረሱልኝ ጥሪዋን በማሰማቷ ምክንያት፤ በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በጋራ በመሆን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማመልከት ፍትሕ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አሰሪዋ “አልደፈርኩም” ብሎ የሕክምና ወረቀት በማቅረብ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ ወጣቷን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፤ ጽ/ቤቱና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከ6 ወራት በላይ በመከራከርና የDNA ምርመራ በማስደረግ በተገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት፤ ወጣቷ የስድስት ወር እርጉዝ መሆኗና የእርሱም ልጅ እንደሆነ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል።

በዚህም መሠረት፤ የወጣቷን እና የልጇንና መብት በማስከበር 64 ሺሕ 800 የባህሬን ዲናር (9 ሚሊዮን 344 ሺሕ 886 ብር) በየአራት ዓመት ክፍያ እንዲከፍል አሰሪው የተስማማ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ አራት ዓመት የሚሆን ቅድመ ክፍያ 14 ሺሕ 200 የባህሬን ዲናር (2 ሚሊዮን 47 ሺሕ 799 ብር) በመቀበል ፍርድ ቤት ፈርሞበት ወጣቷ ፍትህ እንድታገኝ መደረጉን በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አስታውቋል።