Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ የሜሲ ክለብ ኢንተር ሚያሚ የሜሲ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚታይበት የስታዲየም መግቢያ ትኬት ሽያጩ | ሰሌዳ | Seleda

አዲሱ የሜሲ ክለብ ኢንተር ሚያሚ የሜሲ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚታይበት የስታዲየም መግቢያ ትኬት ሽያጩ ደርቶለታል ተባለ።

የአሜሪካው ኢንተር ሚያሚ ከሜክሲኮው ክሩዝ አዙል ጋር በሀምሌ ወር መጨረሻ በሚያደርገው ጨዋታ ዝቅተኛው የመግቢያ ትኬት ዋጋ 29 ዶላር ነበር።

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ሚያሚን እንደሚቀላቀል ካሳወቀ በኋላ ግን የትኬት ዋጋወ በአሜሪካ የእግርኳስ ጨዋታ ታሪክ ታይቶ ማይታወቅ መልኩ እጅግ ንሯል።

ፎርብስ ባወጣው መረጃ መሰረት በሜሲ የመጀመሪያ የኢንተር ሚያሚ ጨዋታ ዝቅተኛው የመግቢያ ትኬት እስከ 459  ዶላር ድረስ እየተሸጠ ነው ብሏል።