Get Mystery Box with random crypto!

በቀጣዩ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር አይፈፀምም ተባለ  መንግስት ከአንድ ወር | ሰሌዳ | Seleda

በቀጣዩ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር አይፈፀምም ተባለ 

መንግስት ከአንድ ወር በኋላ ሃምሌ 2015ዓ.ም በሚጀምረው አዲሱ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት ምንም አይነት የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር እንደማይፈጸም የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ረቂቁን በተመለከተ ለፓርላማው ባቀረቡት ማብራሪያ  የ2016 የመደበኛ በጀት በየመ/ቤቱ ያለውን አዲሱን አደረጃጀት ታሳቢ በማድረግ፣ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባና በውጤታማነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ጠቅሰው በቀጣይ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሠራተኛ ቅጥር እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በጀት መሆኑን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

መንግስት አዘጋጅቶ ባቀረበው የ2016 በጀት ዓመት ካቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች  370.1 ቢሊዮን ብር ፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.4 ቢሊዮን ብር፣ለክልሎች የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ  214  ቢሊዮን ብር፣ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ  14 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል፡፡